ቻይና የቲያንዙ-10 የጭነት መንኮራኩርን ወደ ቲያንጎንግ የጠፈር ጣቢያ ላከች
10:56 11.05.2026 (የተሻሻለ: 11:04 11.05.2026)
© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
ቻይና የቲያንዙ-10 የጭነት መንኮራኩርን ወደ ቲያንጎንግ የጠፈር ጣቢያ ላከች
የሎንግ ማርች 7 ዋይ11 ሮኬት ከቻይናው ደቡባዊ የጠፈር ማረፊያ ከዌንቻንግ ተመጥቋል። መንኮራኩሯ ከመጠቀች ከ10 ደቂቃ በኋላ በተሳካ ሁኔታ ምህዋሯ ውስጥ መግባት ችላለች።
ይህች መንኮራኩር አዲስ ከጠፈር መንኮራኩር ውጪ ለሚደረግ እንቅስቃሴ የሚያገለግል ልብስ ፣ ለጠፈርተኞች የሚውሉ ቁሳቁሶችን፣ ነዳጅ እና ለምርምር የሚሆኑ የሙከራ መሣሪያዎችን ጭናለች። ቲያንዙ-10 ከቲያንጎንግ የጠፈር ጣቢያ ጋር ትስስር ትፈጥራለች።
ይህ ተልዕኮ የ641ኛው የሎንግ ማርች ሮኬት ስምሪት ሲሆን፣ ለቲያንጎንግ ፕሮጀክት ደግሞ 39ኛው ተልዕኮ ነው።
110 ሜትር ኩብ የመኖሪያ ስፍራ ያለው እና ለ15 ዓመታት (እስከ 2038 ) እንዲያገለግል ተደርጎ የተነደፈው ይህ የጠፈር ጣቢያ፣ ከህዳር 2022 ጀምሮ ሙሉ በሙሉ ሥራ ላይ ይገኛል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X