ሩሲያ ለመጀመሪያ ጊዜ እጅግ ቀላል ለሆኑ ሮኬቶች የሚያገለግል የግል የጠፈር ማረፊያ በ2026 ልትገነባ ነው
10:22 11.05.2026 (የተሻሻለ: 10:24 11.05.2026)
© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
ሩሲያ ለመጀመሪያ ጊዜ እጅግ ቀላል ለሆኑ ሮኬቶች የሚያገለግል የግል የጠፈር ማረፊያ በ2026 ልትገነባ ነው
በሩሲያው 'ስፔስ ኢነርጂ' ኩባንያ የሚገነባው የፕሪሞርስኪ ኮስሞድሮም፣ የኩባንያውን የራሱን 'ኦርቢታ' መንኮራኩር (እስከ 250 ኪሎ ግራም ወደ ዝቅተኛው የምድር ምህዋር / 150 ኪሎ ግራም ደግሞ ፀሐይን ተከትሎ ወደሚዞር ምህዋር የማድረስ አቅም ያለው) ጨምሮ፣ ለቀላልና እጅግ ቀላል ለሆኑ ሮኬቶች ተብሎ የተዘጋጀ ነው።
ቦታው የተመረጠው ለሮኬት ጉዞ ምቹ የሆኑ የባሊስቲክ ሁኔታዎችና ደህንነቱ የተጠበቀ የባህር ላይ ማረፊያ ዞኖች ስላለው ነው።
የመጀመሪያው መንኮራኩር እንዲመጠቅ ቀደም ሲል ለ2027 ታቅዶ የነበረ ቢሆንም፣ ፕሮጀክቱ በጊዜ ሰሌዳው መሠረት ከቀጠለ ግን እ.ኤ.አ. በ2026 መጀመሪያ ላይ ሊከናወን ይችላል።
ፕሮጀክቱ ለሌሎች ደንበኞች የንግድ፣ የሳይንስ እና የቴክኖሎጂ ተልዕኮዎችን ሊያገለግል ይችላል፤ ይህም በሩሲያ የጠፈር ኢንዱስትሪ ውስጥ የግል ዘርፉ ተሳትፎ ትልቅ ምዕራፍ ተደርጎ ይወሰዳል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X