አሊኮ ዳንጎቴ በቀን 650 ሺህ በርሜል ነዳጅ የሚያጣራ ፋብሪካ በኬንያ ለመገንባት ማቀዳቸው ተሰማ

ሰብስክራይብ

አሊኮ ዳንጎቴ በቀን 650 ሺህ በርሜል ነዳጅ የሚያጣራ ፋብሪካ በኬንያ ለመገንባት ማቀዳቸው ተሰማ

  ዳንጎቴ የማጣሪያ ፋብሪካው ግንባታ ከ15 ቢሊዮን እስከ 17 ቢሊዮን ዶላር ሊፈጅ እንደሚችል መገመታቸውን መገናኛ ብዙኃን ዘግበዋል።

ዳንጎቴ በሰጡት ቃለ መጠይቅ የኬንያውን ሞምባሳ ከታንዛኒያው ታንጋ ወደብ ጋር በማነጻጸር፤ “ሞምባሳ እጅግ ሰፊና ጥልቅ ወደብ ስላለው ምርጫዬን ወደ ሞምባሳ እያዘነበልኩ ነው” ብለዋል።

የኬንያውን ፕሬዝዳንት ዊልያም ሩቶን ጠቅሰው መገናኛ ብዙኃን እንደዘገቡት፤ ኬንያ፣ ታንዛኒያ እና ሌሎች የምስራቅ አፍሪካ ሀገራት በናይጄሪያው የዳንጎቴ ፋብሪካ ተነሳስተው በታንዛኒያ ታንጋ ወደብ ላይ የጋራ የነዳጅ ማጣሪያ ፋብሪካ ለመገንባት እያሰቡ ነው።

ለተጣሩ የነዳጅ ምርቶች ሙሉ በሙሉ ከመካከለኛው ምስራቅ በሚገቡ ምርቶች ላይ ጥገኛ የሆነችው ምስራቅ አፍሪካ፤ በአሜሪካ-እስራኤል እና በኢራን መካከል ባለው ግጭት ወቅት የታየው ዓይነት የአቅርቦት መስተጓጎል እና የዋጋ አለመረጋጋት ስጋት ተጋርጦባታል።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0