ኢትዮጵያ፣ የደቡብ አፍሪካ መንግሥት በአገሪቱ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ሰላምና ደኅንነት እንዲያረጋግጥ ጠየቀች - የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር

ኢትዮጵያ፣ የደቡብ አፍሪካ መንግሥት በአገሪቱ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ሰላምና ደኅንነት እንዲያረጋግጥ ጠየቀች
ኢትዮጵያ፣ የደቡብ አፍሪካ መንግሥት በአገሪቱ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ሰላምና ደኅንነት እንዲያረጋግጥ ጠየቀች  - Sputnik አፍሪካ, 1920, 10.05.2026
ሰብስክራይብ
ኢትዮጵያ፣ የደቡብ አፍሪካ መንግሥት በአገሪቱ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ሰላምና ደኅንነት እንዲያረጋግጥ ጠየቀች - የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ብርሃኑ ፀጋዬ በኢትዮጵያ የደቡብ አፍሪካ አምባሳደር ኖንሴባ ሎሲ ጋር በደቡብ አፍሪካ በአንዳንድ አካባቢዎች በኢትዮጵያውያን ላይ እየደረሰ ስላለው ጥቃት ውይይት አድርገዋል።

አምባሳደር ብርሃኑ በዜጎች ላይ እየደረሰ ያለው ጥቃት በጥብቅ እንደሚያሳስባቸው ገልጸው፤ የኢትዮጵያውያንን ደህንነትና መብት ማስከበር እንደሚገባ አሳስበዋል።

አምባሳደር ኖንሴባ ሎሲ በበኩላቸው የደቡብ አፍሪካ መንግስት ጥቃቱን እንደሚያወግዝና በውጭ ዜጎች ላይ የሚደርሱ ጥቃቶችን ለመከላከል ቁርጠኛ መሆኑን አረጋግጠዋል።

በተጨማሪም በጉዳዩ ላይ ሰፊ ምርመራ እየተካሄደ መሆኑንና ውጤቱም ለኢትዮጵያ መንግስት እንደሚገለጽ አምባሳደሯ ገልጸዋል።

ሁለቱ ወገኖች በዜጎች ደህንነት፣ በሰነድ አሰጣጥና በሕጋዊ ጥበቃ ዙሪያ ተቀራርበው ለመስራት ተስማምተዋል።

ቀደም ሲል፣ ደቡብ አፍሪካ በውጭ አገር ዜጎች ላይ የሚደርሱ ጥቃቶች በአጠቃላይ ሀገራዊ የወንጀል ድርጊቶች ካር የተያያዙ እንጂ፣ ከመጤ ጠልነት (ዜኖፎቢያ) የመነጨ አለመሆኑን በፕሬዝዳንት ጽ/ቤቷ በኩል ገልፃለች።

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X
አዳዲስ ዜናዎች
0