የኬንያ የመከላከያ ኢንዱስትሪ ልዑክ በኢትዮጵያ የመከላከያ የልማት ፕሮጀክቶችን ጎበኘ

የኬንያ የመከላከያ ኢንዱስትሪ ልዑክ በኢትዮጵያ የመከላከያ የልማት
የኬንያ የመከላከያ ኢንዱስትሪ ልዑክ በኢትዮጵያ የመከላከያ የልማት - Sputnik አፍሪካ, 1920, 10.05.2026
ሰብስክራይብ
የኬንያ የመከላከያ ኢንዱስትሪ ልዑክ በኢትዮጵያ የመከላከያ የልማት ፕሮጀክቶችን ጎበኘ

በብርጋዲየር ጄኔራል ኦስካር ሙልይ የተመራ የኬንያ ከፍተኛ ወታደራዊ ልዑክ፤ በኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት ፋውንዴሽን ስር የሚገኙ የልማት ድርጅቶችን ጎብኝቷል።

ልዑኩ በአዳማ ጋርመንት ኢንዱስትሪ እና በ"ጋሻ" የቤቶች ልማት ፕሮጀክት ያለውን የሥራ እንቅስቃሴ የተመለከተ ሲሆን፤ በተለይም አልባሳትን በሀገር ውስጥ በመተካትና ዘመናዊ የቤት ግንባታ ቴክኖሎጂን በመጠቀም ረገድ እየተከናወነ ባለው ሥራ መደነቁን ተገልጿል።


የመከላከያ ሠራዊት ፋውንዴሽን ዋና ሥራ አስፈፃሚ ሜጀር ጄነራል ደረጀ መገርሳ፣ "ይህ ጉብኝት በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለውን ወታደራዊ ትብብርና የልምድ ልውውጥ ወደ ላቀ ደረጃ የሚያሸጋግር ነው" ማለታቸውን መከላከያ ሠራዊት በማኅበራዊ ሚዲያ ገጹ ላይ አስታውቋል።


የልዑኩ መሪ ብርጋዲየር ጄኔራል ኦስካር ሙልይ በበኩላቸው፣ በወታደራዊ ኢንዱስትሪ ዘርፍ ልምድ ለመጋራት ዝግጁ መሆናቸውን አረጋግጠዋል።

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X
አዳዲስ ዜናዎች
0