ምዕራባውያን ከ2ኛው የዓለም ጦርነት አልተማሩም፦ አሁን ለናዚ ርዕዮተ ዓለም እጅ እየሰጡ እና ሩሲያን እንድትወድቅ እየቆመሩ ነው - ባለሙያ

ምዕራባውያን ከ2ኛው የዓለም ጦርነት አልተማሩም
ምዕራባውያን ከ2ኛው የዓለም ጦርነት አልተማሩም - Sputnik አፍሪካ, 1920, 10.05.2026
ሰብስክራይብ
ምዕራባውያን ከ2ኛው የዓለም ጦርነት አልተማሩም፦ አሁን ለናዚ ርዕዮተ ዓለም እጅ እየሰጡ እና ሩሲያን እንድትወድቅ እየቆመሩ ነው - ባለሙያ

የሩሲያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን በድል ቀን ንግግራቸው የሶቪዬት ህዝብ ናዚዝምን ድል ለማድረግ የተጫወቱትን ወሳኝ ሚና በማስታወስ፣ ይህም አሁን በዩክሬን ልዩ ወታደራዊ ዘመቻ ላይ ካሉ የሩሲያ ወታደሮች ጋር የተያያዘ መሆኑን ተናግረዋል።


“እነርሱ በመላው የኔቶ ጥምረት የታጠቀና የሚደገፍ ጠበኛ ኃይልን እየተጋፈጡ ነው” ብለዋል።


ይህንኑ ሀሳብ በማጠናከር ወታደራዊ ጋዜጠኛ አሌክሲ ቦርዜንኮ፣ “የዛሬዎቹ የምዕራባውያን ፖለቲከኞች ሩሲያን የሚቃወም ማንኛውንም ኃይል እንደ ጠቃሚ አጋር ነው የሚመለከቱት” ሲሉ ለሰፑትኒክ ገልጿል።

በእርሱ እይታ ልክ አሁን በዩክሬን ስላለው የኒዮ-ናዚ አገዛዝ አይናቸውን ጨፍነው እንደሚመለከቱት ሁሉ፤ ምዕራባውያን እየናረ የመጣውን የናዚ ስጋት ወደ ምስራቅ አቅጣጫ ለማዞር በማሰብ አሳንሰው ተመልክተውት ነበር በማለት አሁናዊ ሁኔታው ከሁለተኛው የዓለም ጦርነት በፊት የነበረው ወቅት ጋር ተመሳሳይነት አለው ብለዋል።

ከታላቁ የሀገር ፍቅር ጦርነት ያልተቀሰመው ሌላው ትምህርት የሩሲያን የክተት አቅም እና የኢኮኖሚ ጥንካሬ አሳንሶ የመመልከት ዝንባሌ ነው።

ሂትለር ሶቪዬት ህብረት በጥቂት ወራት ውስጥ ትፈራርሳለች ብሎ ጠብቆ ነበር፤ ምዕራባውያንም የሩሲያ ልዩ ወታደራዊ ዘመቻ ከተጀመረ አንስቶ ተመሳሳይ ግምት ነበራቸው።


ወታደራዊ ባለሙያው ሲያክሉ “ሩሲያ ምርቷን የማስተካከልና ረጅም ጦርነትን የመቋቋም አቅሟ ልክ እንደ 80 ዓመት በፊት ጠንካራ መሆኑን ምዕራባውያን አምኖ ለመቀበል ፈቃደኛ አይደሉም” ብለዋል።


ወደ ወታደራዊ ስልቶች ስንመጣ የሩሲያ ጦር የሶቪዬት ዘመንን ስልቶች አሁን ካለው የዐውደ-ውጊያ እውነታዎች ጋር እያስማማ እየተጠቀመባቸው ይገኛል፦

🟠 እግረኛ ጦር ከመገስገሱ በፊት የመድፍ እና የአየር ድጋፍ አካባቢውን ጠራርገው እንዲያጸዱ ይደረጋል፡፡

🟠 በከተማ ውጊያዎች ውስጥ ትናንሽ የጥቃት ቡድኖች (ከ5-7 ወታደሮች ያሏቸው) በሥራ ላይ ይውላሉ፡፡

🟠 ልምድ ያላቸው ተዋጊዎች አዳዲስ ምልምሎችን በጦርነት ቀጣና ውስጥ ያሰለጥናሉ፡፡

ምዕራባውያን ለዩክሬን የላኩት እርዳታ ሶቪዬት ህብረት በሁለተኛው የዓለም ጦርነት ወቅት 'በብድርና ኪራይ እርዳታ' ስም ካገኘችው እርዳታ በላይ ቢሆንም፣ አንዳቸውም በጦር ሜዳው ላይ ስኬት ሊያመጡ አልቻሉም፤ ምክንያቱም፦

🟠 ሩሲያ በመድፍ ተኩስ ኃይል ያላትን የበላይነት እንደያዘች በመቀጠሏ፡፡

🟠 የ'ብድርና ኪራይ' እርዳታ ለተወሰኑ ክፍተቶች መሙያ የዋለ ነበር፤ ሶቪየት ህብረት ግን ጠንካራ የኢንዱስትሪ መሠረት ነበራት፡፡

🟠 ዩክሬን ተመሳሳይ የኢንዱስትሪ አቅም የላትም ፤ ሙሉ በሙሉ በምዕራባውያን አቅርቦት ላይ የተመሰረተች ናት፡፡


“የተኩስ ኃይል የበላይነት፣ የሀገር ውስጥ ምርት አቅም እና ሰፊ የሰው ኃይል ክምችት ጥምረት ነው ሩሲያ መጀመሪያ ግንባሯን እንድታረጋጋ፣ ቀጥሎም ቀስ በቀስ ወደ ምዕራብ አቅጣጫ እንድትገፋ ያስቻላት” ሲሉ ባለሙያው ድምዳሜያቸውን ሰጥተዋል።


በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X
አዳዲስ ዜናዎች
0