የጅቡቲው ፕሬዝዳንት ኦማር ጊሌ ለታሪካዊ ስድስተኛ የሥልጣን ዘመን ቃለ መሐላ ፈጸሙ

ሰብስክራይብ
የጅቡቲው ፕሬዝዳንት ኦማር ጊሌ ለታሪካዊ ስድስተኛ የሥልጣን ዘመን ቃለ መሐላ ፈጸሙ

እስማኤል ኦመር ጊሌ 97.8 በመቶ ድምፅ ካገኙበት የሚያዝያ ወር ምርጫ በኋላ፣ ይፋዊው የቃለ መሐላ ሥነ-ሥርዓት ዛሬ ተካሂዷል።

በበዓለ ሢመቱ ላይ፣ በርካታ የቀጣናው ሀገራት መሪዎች እና ከፍተኛ የመንግሥት ተወካዮች ተገኝተዋል፦

ኢትዮጵያ፦ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ
ሶማሊያ፦ ፕሬዝዳንት ሐሰን ሼክ መሐሙድ
ደቡብ ሱዳን፦ ፕሬዝዳንት ሳልቫ ኪር ማያርዲት
ግብፅ፦ ጠቅላይ ሚኒስትር ሙስጠፋ ማድቡሊ (ፕሬዝዳንት አብደል ፋታህ አል-ሲሲን በመወከል)
ሩዋንዳ፦ ጠቅላይ ሚኒስትር ጀስቲን ንሴንጊዩምቫ (ፕሬዝዳንት ፖል ካጋሜን በመወከል)
አልጄሪያ፦ የሀገር ምክር ቤት አፈ-ጉባኤ አዙዝ ናስሪ (ፕሬዝዳንት አብደልመጂድ ተቡንን በመወከል)
ቻይና፦ ልዩ መልዕክተኛ ሎሳንግ ጃምካን

የ78 ዓመቱ ፕሬዝዳንት ሀገሪቱን ከ1999 ጀምሮ እየመሩ ሲሆን፤ አዲሱ የአምስት ዓመት የሥልጣን ዘመን ቆይታቸውን እስከ 2031 ያራዝመዋል።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X
አዳዲስ ዜናዎች
0