አርቲስት ተገኔ ቁምቢ የኢትዮጵያን የጥበብና የባህል ሀብት በጣሊያን ቬኒስ እያስተዋወቀ ነው
16:29 08.05.2026 (የተሻሻለ: 16:49 08.05.2026)
© Sputnik
ሰብስክራይብ
አርቲስት ተገኔ ቁምቢ የኢትዮጵያን የጥበብና የባህል ሀብት በጣሊያን ቬኒስ እያስተዋወቀ ነው
በጣሊያን ቬነስ ከተማ በሚካሄደው 61ኛው ዓለም አቀፍ የአርት ኤግዚቢሽን ላይ፤ ኢትዮጵያ በራሷ ፓቪሊዮን (መካነ-ጥበብ) የጥበብ እና የቱሪዝም ሀብቷን ለዓለም እያስተዋወቀች ትገኛለች።
በአርቲስት ተገኔ ቁምቢ የተዘጋጀውና የኢትዮጵያን ብሔሮችና ብሔረሰቦች ማንነት የሚወክለው ይህ የጥበብ ሥራ፤ በጣሊያን የኢትዮጵያ አምባሳደር ደሚቱ ሀምቢሳ እና የፓቪሊዮኑ ኩሬተር ፕሮፌሰር አበባው አያሌው በተገኙበት ትናንት በይፋ ተመርቋል።
በመክፈቻው ሥነ-ስርዓት ላይ የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ "መደመር" መጽሐፍ የእንግሊዝኛ እትም ለቬነስ ከተማ አስተዳደር ቤተ-መጻሕፍት በስጦታ የተበረከተ ሲሆን፤ የኢትዮጵያ ቡና አፈላልና ባህላዊ ምግቦችም ለታዳሚዎች ቀርበዋል።
ኤግዚቢሽኑ እስከ መጪው ህዳር 2026 ለተከታታይ ስድስት ወራት ለጎብኚዎች ክፍት ሆኖ እንደሚቆይ የቱሪዝም ሚኒሰቴር በማኅበራዊ ትስስር ገፁ አመላክቷል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X