ባለፉት ዘጠኝ ወራት 9,600 ኪሎ ሜትር ገደማ የሚሸፍን አዲስ የኤሌክትሪክ መስመር ዝርጋታ ተከናውኗል - የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት

9,600 ኪሎ ሜትር ገደማ የሚሸፍን አዲስ የኤሌክትሪክ መስመር ዝርጋታ
9,600 ኪሎ ሜትር ገደማ የሚሸፍን አዲስ የኤሌክትሪክ መስመር ዝርጋታ  - Sputnik አፍሪካ, 1920, 08.05.2026
ሰብስክራይብ
ባለፉት ዘጠኝ ወራት 9,600 ኪሎ ሜትር ገደማ የሚሸፍን አዲስ የኤሌክትሪክ መስመር ዝርጋታ ተከናውኗል - የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት

አገልግሎቱ፣ በበጀት ዓመቱ ሦስተኛ የሩብ ዓመታት 3 ሺህ 518 ኪ.ሜ የመካከለኛ መስመር፣ 6 ሺህ 69 ኪ.ሜ ደግሞ የዝቅተኛ መስመር ዝርጋታ ማከናወኑን አስታውቋል፡፡

በተጨማሪ አስተማማኝ የኃይል አቅርቦት አቅምን የሚያሳድጉ 3 ሺህ 683 አዳዲስ ትራንስፎርመሮች መተከላቸውን አገልግሎት አመላክቷል።

የኃይል መቆራረጥን ለመቀነስ በ62 ሺህ 274 ኪሎ ሜትር ነባር መስመሮችና በ67 ሺህ በላይ ትራንስፎርመሮች ላይ የቅድመ መከላከል ጥገና መካሄዱም ተጠቁሟል።

ተቋሙ ያረጁ መስመሮችን በመቀየርና የቴክኒክ ብልሽቶችን በፍጥነት በመጠገን የኃይል መቆራረጥ ድግግሞሽንና የቆይታ ጊዜን መቀነስ መቻሉን ገልጿል።

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X
አዳዲስ ዜናዎች
0