የአሽከርካሪዎች ብቃት መመዘኛ ዲጂታል ሥርዓት ወደ ሥራ ሊገባ ነው

የአሽከርካሪዎች ብቃት መመዘኛ ዲጂታል ሥርዓት ወደ ሥራ ሊገባ ነው
የአሽከርካሪዎች ብቃት መመዘኛ ዲጂታል ሥርዓት ወደ ሥራ ሊገባ ነው - Sputnik አፍሪካ, 1920, 08.05.2026
ሰብስክራይብ
የአሽከርካሪዎች ብቃት መመዘኛ ዲጂታል ሥርዓት ወደ ሥራ ሊገባ ነው

የብቃት መመዘኛውን በዲጂታል ሥርዓት ለማከናወን የሚያስችል አዲስ መተግበሪያ ተዘጋጅቶ መጠናቀቁን የትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስቴር አስታውቋል።

🪪 ከፋይዳ ዲጂታል መታወቂያ ጋር ተሳስሮ የተዘጋጀው ይህ ሲስተም፤ አሽከርካሪዎች ባሉበት ቦታ ሆነው ምዝገባ እንዲያካሂዱ፣ የፈተና ቦታና ሰዓት እንዲያውቁ እንዲሁም ውጤታቸውን በፈጣን መልዕክት እንዲያገኙ ያስችላል።

⏳ የሥርዓቱ ትግበራ አሽከርካሪዎችን መዝግቦ፣ አሰልጥኖና ፈትኖ የብቃት ማረጋገጫ ለመስጠት የሚያስችል ሲሆን፤ የቅድመ ዝግጅት ሥራዎች መጠናቀቃቸውንና በቅርቡ አገልግሎት መስጠት እንደሚጀምር የትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስትር ዴኤታ በርኦ ሀሰን ገልጸዋል።

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X
አዳዲስ ዜናዎች
0