የአሜሪካ እና ኢራን የተኩስ አቁም ስምምነት እስካሁን እንደጸና ነው - ትራምፕ

ሰብስክራይብ

የአሜሪካ እና ኢራን የተኩስ አቁም ስምምነት እስካሁን እንደጸና ነው - ትራምፕ

ኢራናዊያን ምንጮች የአሜሪካ አውዳሚ መርከቦች ዛሬ ማለዳ ላይ የኢራን የነዳጅ ጫኝ መርከብ መምታታቸውን ቢገልጹም፣ የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ግን ከኢራን ጋር ያለው የተኩስ አቁም ስምምነት አሁንም ባለበት መቀጠሉን ተናግረዋል።

"ፕሬዝዳንቱ የተኩስ አቁሙ አሁንም ቀጥሏል ወይ ተብለው በጋዜጠኞች ለቀረበላቸው ጥያቄ፣ “አዎ፣ ቀጥሏል። ዛሬ እኛን ለመተንኮስ ሞክረው ነበር፤ እኛ ግን አይቀጡ ቅጣት ቀጥተናቸዋል” ሲሉ ምላሽ ሰጥተዋል።

ትራምፕ አክለውም ንግግሮች “በጣም በጥሩ ሁኔታ ላይ ናቸው” ቢሉም፣ ስምምነት የማይፈረም ከሆነ ግን ኢራን ለሚያስከትለው ውጤት ዝግጁ መሆን እንዳለባት አስጠንቅቀዋል።

“ስምምነቱ የማይፈረም ከሆነ፣ እጅግ በጣም ከባድ ዋጋ ይከፍላሉ” ሲሉ ገልፀዋል።

እነዚህ ንግግሮች የተሰሙት በሆርሙዝ ወሽመጥ አካባቢ ውጥረት በነገሰበት እና የአሜሪካ እና የኢራን ኃይሎች ስለተሳተፉባቸው ግጭቶች የሚወጡ መረጃዎች እርስ በእርስ እየተጋጩ ባሉበት ወቅት ነው።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0