በልዩ ወታደራዊ ዘመቻ ያሉ ሁሉም የሩሲያ ወታደራዊ ቡድኖች በተኩስ አቁም ምክንያት ከሚያዝያ 30 - ግንቦት 2 ወታደራዊ እንቅስቃሴ ያቆማሉ: መከላከያ ሚኒስቴር
19:41 07.05.2026 (የተሻሻለ: 20:21 07.05.2026)

ሰብስክራይብ
በልዩ ወታደራዊ ዘመቻ ቀጣና ውስጥ የሚገኙ ሁሉም የሩሲያ ወታደራዊ ቡድኖች በተኩስ አቁም ስምምነት ምክንያት ከሚያዝያ 30 እስከ ግንቦት 2 ወታደራዊ እንቅስቃሴያቸውን ያቆማሉ - የመከላከያ ሚኒስቴር
ሚኒስቴሩ በመግለጫው ያነሳቸው ተጨማሪ ነጥቦች፦
በተኩስ አቁም ወቅት፣ በዩክሬን ግዛት ውስጥ በሚገኙ የዩክሬን ጦር የስምሪት ቦታዎች፣ ከወታደራዊ-ኢንዱስትሪ ማምረቻዎች ጋር በተያያዙ ተቋማት እና በጦር ኃይሎች ላይ የሚፈጸሙ ጥቃቶች ይቆማሉ።
የዩክሬን ጦር በልዩ ወታደራዊዘመቻ ቀጣና ውስጥ የተኩስ አቁም ስምምነቱን ከጣሰ ወይም በሕዝብ በሚኖርባቸው አካባቢዎች እና ተቋማት ላይ ጥቃት ለመሰንዘር ከሞከረ፣ ሩሲያ ተመጣጣኝ ምላሽ ትሰጣለች።
ዩክሬን በሞስኮ የሚካሄደውን የድል ቀን አከባበር ለማደናቀፍ ከሞከረች፣ ሩሲያ በማዕከላዊ ኪዬቭ ላይ ከፍተኛ ሚሳኤል ጥቃት ትፈጽማለች፡፡
"በኪዬቭ የሚገኙ ሲቪሎች እና የውጭ ሀገራት ዲፕሎማሲያዊ ተልዕኮ ሠራተኞች ከተማዋን በጊዜ ለቀው መውጣት እንደሚያስፈልጋቸው በድጋሚ እናስጠነቅቃለን" ሲል የሩሲያ መከላከያ ሚኒስቴር አስታውቋል።
በእንግሊዘኛ ያንብቡ
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X