ኬንያ ከሙከራ ደረጃ ወደ ሙሉ የንግድ ነዳጅ ምርት ተሸጋገረች - በቀን 50 ሺህ በርሜል የማምረት ግብ ተቀምጧል

ሰብስክራይብ

ኬንያ ከሙከራ ደረጃ ወደ ሙሉ የንግድ ነዳጅ ምርት ተሸጋገረች - በቀን 50 ሺህ በርሜል የማምረት ግብ ተቀምጧል

​ምርቱ በቀን በ20 ሺህ በርሜል የሚጀመር ሲሆን፣ ቀስ በቀስ ወደ 50 ሺህ በርሜል ከፍ ይላል ሲሉ የኢነርጂ ካቢኔ ጸሐፊ ኦፒዮ ዋንዳዪ ለሕግ አውጪዎች ተናግረዋል።

​ ኬንያ እስከ መጪው ዓመት አጋማሽ ድረስ በቱርካና ከሚገኙት የደቡብ ሎኪቻር የነዳጅ ቦታዎች የንግድ ነዳጅ ምርት ትጀምራለች ተብሎ ይጠበቃል፤ ምርቱም ወደ አፍሪካ ነዳጅ አምራች ሀገራት ጎራ እንድትቀላቀል ያደርጋታል።

የነዳጅ ማጣሪያው ማጣሪያ እውነታ፦ የነዳጅ ምርቱ አዋጭ እንደሆነ ቢታመንም፣ ማጣሪያው ግን ትልልቅ መሰናክሎች አሉበት፡፡ እነሱም፦

​▫ የሞምባሳ የድፍድ ነዳጅ ማጣሪያ ጣቢያ አሁን ባለው የምርት ደረጃ በኢኮኖሚ ረገድ አዋጭ እንዳልሆነ ተደርሶበታል።

▫ ዘላቂ የድፍድፍ ነዳጅ ማጣሪያ ሥራ ለማከናወን በቀን ከ100 ሺህ እስከ 500 ሺህ በርሜል ምርት ያስፈልጋል።

▫ የኬንያ የመጀመሪያ ደረጃ የማምረት አቅም ግን ከዚህ መስፈርት በታች ነው።

የምስራቅ አፍሪካ ቀጣናዊ ውህደት፣ በቀጣይ ደረጃዎች ላይ የሚደረጉ ኢንቨስትመንቶች በሚከተሉት ላይ የተመሠረቱ ናቸው፦

​▫ በወደፊት የምርት ዕድገት እና

▫ ቀጣናዊ ውህደት።

​ ኬንያ፣ ታንዛኒያ እና ኡጋንዳ ከውጭ የሚገባ ነዳጅ ላይ ያላቸውን ጥገኝነት ለመቀነስ የጋራ ቀጣናዊ የድፍድፍ ነዳጅ ማጣሪያ ጣቢያ ስለመገንባት በድጋሚ እየመከሩ ቢሆንም፣ እስካሁን ግን ምንም ዓይነት ይፋዊ ስምምነት ላይ አልተደረሰም።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0