የሕንድ ከፍተኛ ወታደራዊ ልዑክ በኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት የሰላም ማስከበር ማዕከል እና ዋር ኮሌጅ ጉብኝት አደረገ
15:36 07.05.2026 (የተሻሻለ: 15:59 07.05.2026)

ሰብስክራይብ
የሕንድ ከፍተኛ ወታደራዊ ልዑክ በኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት የሰላም ማስከበር ማዕከል እና ዋር ኮሌጅ ጉብኝት አደረገ
በሜጀር ጄኔራል ራቭሩፕ ሲንግ የተመራው ይህ ልዑክ፣ ከሰላም ማስከበር ማዕከል አዛዥ ሜጀር ጄኔራል አዳምነህ መንግሥቴ ጋር በሁለቱ ሀገራት የሰላም ማስከበር ተሳትፎ፤ በትምህርትና አጠቃላይ እንቅስቃሴ ዙሪያ ውይይት አድርገዋል፡፡
አዛዡ ኢትዮጵያ የሰላም ማስከበር ተልዕኮን በሥልጠና እና በስትራቴጂ በመከወን ሽብርተኝነትን እና ፅንፈኝነትን በመታገል ከፍተኛ ሚና እየተወጣች እንደምትገኝ ተናግረዋል፡፡
ልዑካን ቡድኑ በዋር ኮሌጅ ባደረገው ጉብኝት፣ ኮሌጁ በዓለም አቀፋዊና ቀጣናዊ እና አኅጉራዊ ፀጥታና ደህንነት ጉዳዮች ዙሪያ ለመከላከያ አመራሮች እና ለአፍሪካ ሀገራት ጭምር ትምህርት እየሰጠ መሆኑን በኮሌጁ አዛዥ ብርጋዲየር ጄኔራል ጥላሁን ደምሴ ገልጻ ተደርጎለታል፡፡
በስተመጨረሻም የሁለቱ ሀገራት ጄኔራል መኮንኖች የሀገራቸውን አርማ የያዘ ስጦታ በመለዋወጥ ወዳጅነታቸውን አጽንተዋል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X