የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ከቻይናው ሆፕ ሜዲካል ጋር የኢንቨስትመንት ስምምነት ተፈራረመ

የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ከቻይናው ሆፕ ሜዲካል
የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ከቻይናው ሆፕ ሜዲካል - Sputnik አፍሪካ, 1920, 07.05.2026
ሰብስክራይብ
የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ከቻይናው ሆፕ ሜዲካል ጋር የኢንቨስትመንት ስምምነት ተፈራረመ

ሆፕ ሜዲካል ኮንሱመብልስ ማኑፋክቸሪንግ ግንባታውን በ7 ወራት ውስጥ አጠናቅቆ ወደ ሥራ ሲገባ፣ 95 በመቶ የሚሆነውን ምርቱን ለሀገር ውስጥ ገበያ በማቅረብ የገቢ ምርትን ለመተካት አልሟል።

የኮርፖሬሽኑ ዋና ሥራ አስፈፃሚ ፍስሃ ይታገሱ፣ ባለሃብቶችን በተለይም በፋርማሲዩቲካል ዘርፍ እንዲሰማሩ ለማድረግ በኢትዮጵያ የቻይና ኤምባሲ የሚያደርገውን ድጋፍ እንዲያጠናክር ጠይቀዋል፡፡ የኮርፖሬሽኑ ሠራተኞች መሠረታዊ የቻይና ቋንቋ ሥልጠና መውሰዳቸው ግንኙነቱን ያቀላጥፈዋል ሲሉ አክለዋል።

በኢትዮጵያ የቻይና አምባሳደር ቼን ሃይ የቻይና ባለሀብቶች በፋርማሲዩቲካል ዘርፍ በስፋት እንዲሰማሩ ድጋፋቸውን እንደሚቀጥሉ አረጋግጠዋል።

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X
አዳዲስ ዜናዎች
0