የአጥፍቶ ጠፊ ተሽከርካሪ በማሊ ፕሬዝዳንት አሲሚ ጎይታ መኖሪያ ቤት ላይ ጥቃት ለመሰንዘር መሞከሩን ጦር ሰራዊቱ ገለጸ
14:41 07.05.2026 (የተሻሻለ: 14:44 07.05.2026)
© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
የአጥፍቶ ጠፊ ተሽከርካሪ በማሊ ፕሬዝዳንት አሲሚ ጎይታ መኖሪያ ቤት ላይ ጥቃት ለመሰንዘር መሞከሩን ጦር ሰራዊቱ ገለጸ
የጦር ሰራዊቱ የህዝብ ግንኙነት ምክትል ዳይሬክተር ጅብሪላ ማኢጋ፣ ባለፈው ሚያዚያ 17 የተፈጸመውን የሽብር ጥቃት ተከትሎ በወቅታዊ የደህንነት ሁኔታ ላይ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ፤ ወታደሮቹ ስጋቱን ለመቆጣጠር እና ተሽከርካሪውን ከጥቃት ውጭ ለማድረግ “ጠንካራ ምላሽ” ሰጥተዋል ብለዋል።
እንደ ወታደራዊ ባለስልጣኑ ገለፃ፣ ሌላ የአጥፍቶ ጠፊ ተሽከርካሪ በሚኒስትር ሳዲዮ ካማራ መኖሪያ ቤት ላይ ጥቃት ለመሰንዘር ታቅዶ ነበር።
ማኢጋ እንደተናገሩት፣ ጥቃት አድራሾቹ በርካታ የአጥፍቶ ጠፊ ተሽከርካሪዎችን ያዘጋጁ ሲሆን፤ ከሀገር ውስጥ እና ከውጭ ድጋፍ ተደርጎላቸው ሊሆን ይችላል። የጥቃቱ ስፋት እና ጥቅም ላይ የዋሉት ዘዴዎች ሽብርተኞቹ የውጭ እና የሀገር ውስጥ ድጋፍ እንዳላቸው ያሳያል ብለዋል።
በተካሄደው ኦፕሬሽን በርካታ ሽብርተኞች የተደመሰሱ ሲሆን፤ ተሽከርካሪዎች እና ሞተር ሳይክሎችም በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ሰራዊቱ አክሎ ገልጿል።
ቪዲዮው የሩሲያ አፍሪካ "ኮርፕስ" እና የማሊ ጦር ባማኮን ለመዝጋት የተደረገውን ሙከራ ሲያከሽፉ ያሳያል
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X