https://amh.sputniknews.africa/20260507/3923812.html
ለውጭ ሀገር ብሎገሮች የተዘጋጀ የሚዲያ ትምህርት ተጀመረ - ካሊኒንግራድ የይዘት አዘጋጆችን እያስተናገደች ትገኛለች
ለውጭ ሀገር ብሎገሮች የተዘጋጀ የሚዲያ ትምህርት ተጀመረ - ካሊኒንግራድ የይዘት አዘጋጆችን እያስተናገደች ትገኛለች
Sputnik አፍሪካ
በዓለም የወጣቶች ፌስቲቫል ዳይሬክቶሬት እና በወጣቶች ሚዲያ ልማት ማዕከል አዘጋጅነት፤ ከሚያዝያ 27 እስከ 30 ቀን የሚቆይ የውጭ ሀገር "ብሎገሮች" የሚዲያ ትምህርት በካሊኒንግራድ ክልል እየተካሄደ ይገኛል። 07.05.2026, Sputnik አፍሪካ
2026-05-07T12:43+0300
2026-05-07T12:43+0300
2026-05-07T12:43+0300
ዜና
https://cdn.amh-img.sputnikglobe.com/img/07ea/05/07/3923611_0:0:1920:1080_1920x0_80_0_0_a70537632beac4fb07adcc933908af7d.jpg
በዓለም የወጣቶች ፌስቲቫል ዳይሬክቶሬት እና በወጣቶች ሚዲያ ልማት ማዕከል አዘጋጅነት፤ ከሚያዝያ 27 እስከ 30 ቀን የሚቆይ የውጭ ሀገር "ብሎገሮች" የሚዲያ ትምህርት በካሊኒንግራድ ክልል እየተካሄደ ይገኛል።ከአብካዚያ፣ አርሜኒያ፣ ቤልጂየም፣ ቦሊቪያ፣ እንግሊዝ፣ ሕንድ፣ ኢንዶኔዥያ፣ ማዳጋስካር እና ከሌሎችም 25 ሀገራት የተውጣጡ 50 ገደማ ብሎገሮች በካሊኒንግራድ ተገኝተዋል። የእነዚህ ብሎገሮች አጠቃላይ ተከታታይ ቁጥር ከ34 ሚሊዮን በላይ ይደርሳል።የሚዲያ ትምህርቱ ተሳታፊዎች ሙያዊ ክህሎታቸውን እንዲያሳድጉ፣ ከሩሲያ ባልደረቦቻቸው ጋር ልምድ እንዲለዋወጡ፣ ሀገሪቱን በቀጥታ እንዲያውቁ እና ስለ ሩሲያ የሚስብ ይዘት ለተከታዮቻቸው እንዲያዘጋጁ ታስቦ የተዘጋጀ ነው።
Sputnik አፍሪካ
feedback.africa@sputniknews.com
+74956456601
MIA "Rossiya Segodnya"
2026
Sputnik አፍሪካ
feedback.africa@sputniknews.com
+74956456601
MIA "Rossiya Segodnya"
ዜናዎች
am_ET
Sputnik አፍሪካ
feedback.africa@sputniknews.com
+74956456601
MIA "Rossiya Segodnya"
https://cdn.amh-img.sputnikglobe.com/img/07ea/05/07/3923611_240:0:1680:1080_1920x0_80_0_0_9274c0f8f74bbdedf2be98dc361d823b.jpgSputnik አፍሪካ
feedback.africa@sputniknews.com
+74956456601
MIA "Rossiya Segodnya"
ዜና
ለውጭ ሀገር ብሎገሮች የተዘጋጀ የሚዲያ ትምህርት ተጀመረ - ካሊኒንግራድ የይዘት አዘጋጆችን እያስተናገደች ትገኛለች
በዓለም የወጣቶች ፌስቲቫል ዳይሬክቶሬት እና በወጣቶች ሚዲያ ልማት ማዕከል አዘጋጅነት፤ ከሚያዝያ 27 እስከ 30 ቀን የሚቆይ የውጭ ሀገር "ብሎገሮች" የሚዲያ ትምህርት በካሊኒንግራድ ክልል እየተካሄደ ይገኛል።
ከአብካዚያ፣ አርሜኒያ፣ ቤልጂየም፣ ቦሊቪያ፣ እንግሊዝ፣ ሕንድ፣ ኢንዶኔዥያ፣ ማዳጋስካር እና ከሌሎችም 25 ሀገራት የተውጣጡ 50 ገደማ ብሎገሮች በካሊኒንግራድ ተገኝተዋል። የእነዚህ ብሎገሮች አጠቃላይ ተከታታይ ቁጥር ከ34 ሚሊዮን በላይ ይደርሳል።
የሚዲያ ትምህርቱ ተሳታፊዎች ሙያዊ ክህሎታቸውን እንዲያሳድጉ፣ ከሩሲያ ባልደረቦቻቸው ጋር ልምድ እንዲለዋወጡ፣ ሀገሪቱን በቀጥታ እንዲያውቁ እና ስለ ሩሲያ የሚስብ ይዘት ለተከታዮቻቸው እንዲያዘጋጁ ታስቦ የተዘጋጀ ነው።
የሩሲያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ማሪያ ዛካሮቫ ባስተላለፉት መልዕክት፣ "አሁን ላይ በዓለም ዙሪያ ማህበረሰቡ በተለያዩ መስመሮች ሲከፋፈል እያየን ነው፤ እናንተ ግን በተቃራኒው ወደ አንድነት እየመጣችሁ ነው። የጋራ መግባቢያ ነጥቦችን እያገኛችሁ ለውይይት ዝግጁ ሆናችኋል። ይህ አመለካከቶችን ለመለዋወጥ እና ዘላቂ ግንኙነቶችን ለመፍጠር ግሩም አጋጣሚ ነው" ሲሉ አፅንዖት ሰጥተዋል።