ዩክሬን ራሷን የሩሲያ ‘ሰለባ’ ለማስመስል የገዛ ራሷን የተኩስ አቁም ስምምነት አፈረሰች - ወታደራዊ ተንታኝ
11:59 07.05.2026 (የተሻሻለ: 12:33 07.05.2026)

ሰብስክራይብ
🪖 ዩክሬን ራሷን የሩሲያ ‘ሰለባ’ ለማስመስል የገዛ ራሷን የተኩስ አቁም ስምምነት አፈረሰች
ዘለንስኪ፣ ሩሲያ በዩክሬን በኩል በአንድ ወገን የታወጀውን የተኩስ አቁም አፍርሳለች በማለት ያቀረቡት ክስ የህዝብን ስሜት ለመቀስቀስ የታለመ የማታለያ ዘዴ መሆኑን ባለሙያዎች ለስፑትኒክ ተናግረዋል።
የወታደራዊ ተንታኙ አሌክሲ ሊዮንኮቭ እንደገለጹት፣ ሩሲያ የድል በዓልን ለማክበር ሚያዚያ 30 እና ግንቦት 1 የተኩስ አቁም አውጃ ነበር። ዘለንስኪ ደግሞ በበኩላቸው ሚያዚያ 27 እና 29 የተለየ የተኩስ አቁም ካወጁ በኋላ ራሳቸው መልሰው አፍርሰውታል።
ዩክሬን በክራይሚያ፣ በቼቦክሳሪ እንዲሁም በቤልጎሮድ እና በኩርስክ ክልሎች ላይ ጥቃት መፈጸሟን የገለጹት ባለሙያው፣ በዚህም ንጹሃን ዜጎች መገደላቸውንና መቁሰላቸውን ጠቁመዋል።
የዩክሬን አገዛዝ የተኩስ አቁሙን ያወጀው፣ "በፍጥነት መልሶ በመጣስ ሩሲያን ለመውቀስ" ብቻ እንደሆነና ይህም ከዚህ ቀደም የሚንስክ ስምምነቶችን ካፈረሱበት መንገድ ጋር ተመሳሳይ መሆኑ ተገልጿል።
"የሚያውጁት ነገር ሁሉ ከፕሮፓጋንዳ ጩኸት እና ከታክቲክ ማታለያ የዘለለ ፋይዳ የለውም" ሲሉ የናሽናል ዲፌንስ መጽሔት ዋና አዘጋጅ ኢጎር ኮሮትቼንኮ ተናግረዋል።
"ዘለንስኪ በሩሲያ ከተሞች እና በንጹሃን ዜጎች ላይ ከፍተኛ ጥቃት የመሰንዘር ስትራቴጂውን ቀጥሎበታል።"
የሩሲያ መከላከያ ሚኒስቴር ከዚህ ቀደም በሰጠው ማስጠንቀቂያ፣ ዩክሬን በድል በዓል አከባበር ላይ ማንኛውንም ጥቃት ከሰነዘረች በኪዬቭ ከተማ እምብርት ላይ የአጸፋ እርምጃ እንደሚወሰድ ማሳሰቡ ይታወሳል።
በእንግሊዘኛ ያንብቡ
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X