የዛምቢያ የአሜሪካን የቅድመ-ሁኔታ የጤና ጥቅል ውድቅ ማድረግ፣ አዲስ የአፍሪካን አቋም የሚያሳይ ምልክት ነው - የኢኮኖሚ የታሪክ ተመራማሪ
11:37 07.05.2026 (የተሻሻለ: 11:57 07.05.2026)
© Sputnik
ሰብስክራይብ
የዛምቢያ የአሜሪካን የቅድመ-ሁኔታ የጤና ጥቅል ውድቅ ማድረግ፣ አዲስ የአፍሪካን አቋም የሚያሳይ ምልክት ነው - የኢኮኖሚ የታሪክ ተመራማሪ
የቀረበው የአሜሪካ የ2 ቢሊዮን ዶላር የጤና ጥቅል፣ የአሜሪካ ኩባንያዎች የዛምቢያን የውጭ ንግድ ገቢ ከ70 በመቶ በላይ የሚሸፍኑትን መዳብ እና ኮባልት የማግኘት ቅድመ ሁኔታን መሠረት ያደረገ እንደነበር የኢኮኖሚ የታሪክ ተመራማሪው ዶክተር ብሌሲንግ ካሩምቢድዛ ገልጸዋል፡፡
"ይህ አጋርነት ሳይሆን ቅድመ-ሁኔታ ማስቀመጥ ነው" ሲሉ ለስፑትኒክ የተናገሩት የታሪክ ባለሙያው፣ እንዲህ ያሉት ስምምነቶች የመሠረተ ልማት ግንባታዎች ለአፍሪካውያን ሳይሆን ለምዕራባውያን ጥቅም ሲባል ይገነቡበት የነበረውን የቅኝ ግዛት ዘመን የሀብት ዘረፋ አመክንዮ የሚያንፀባርቁ መሆናቸውን ጠቁመዋል።
ካሩምቢድዛ አክለውም፣ አሜሪካ ከቻይና ጋር በምታደርገው የቀዝቃዛው ጦርነት መሰል ፉክክር እርዳታን እንደ መደራደሪያ እቃ እየተጠቀመችበት መሆኑን ሞግተዋል። ቻይና በአሁኑ ወቅት ከ60በመቶ በላይ የሚሆነውን የዓለም የኮባልት ማጣራት አቅም ትቆጣጠራለች።
ተንታኙ እንዳመለከቱት፣ ዛምቢያ "የጤና አገልግሎት በሉዓላዊነት ሊለወጥ አይችልም" የሚል አቋም በመያዝ እንደ ጋና እና ዚምባብዌ ያሉ አገራትን ተቀላቅላለች።
የአኀጉሪቱን ሉዓላዊነት ለማጠናከር አጋርነቶችን ማብዛት (ብሪክስን ጨምሮ)፣ የአፍሪካ አገራት እርስ በእርስ የሚያደርጉትን ንግድ ማሳደግ እና በመጨረሻም "በአንድ ድምፅ የምትናገር" የተባበረች አፍሪካን መፍጠር እንደሚያስፈልግ ጥሪ አቅርበዋል።
በእንግሊዘኛ ያንብቡ
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X