የዛምቢያ ቅድመ ሁኔታዎች ያሉትን የአሜሪካ የጤና ስምምነት ውድቅ ማድረጓ፣ እርዳታን "በማንኛውም ዋጋ" ከመቀበል መውጣቷን ያሳያል - ኬንያዊ ተንታኝ

ሰብስክራይብ
የዛምቢያ ቅድመ ሁኔታዎች ያሉትን የአሜሪካ የጤና ስምምነት ውድቅ ማድረጓ፣ እርዳታን "በማንኛውም ዋጋ" ከመቀበል መውጣቷን ያሳያል - ኬንያዊ ተንታኝ

​ የዛምቢያ መንግሥት ከወሳኝ ማዕድናት ስምምነት ጋር የተያያዘውን የሁለት ቢሊዮን ዶላር፣ የአሜሪካ የጤና ስምምነት ለመፈረም ፈቃደኛ አለመሆኑ ለአፍሪካ ሉዓላዊነት ወሳኝ ለውጥ ማሳያ መሆኑን ኬንያዊው የመንግሥት አስተዳደር ባለሙያ ፕሮፌሰር ፍሬድሪክ ኦንያንጎ ኦጎላ ገለጹ።


"ይህ ድርጊት 'በማንኛውም ዋጋ ካፒታል እንፈልጋለን' ከሚለው አስተሳሰብ ወደ 'ካፒታል የሀገርን ሉዓላዊነት እና የረጅም ጊዜ እሴትን ማክበር አለበት' ወደሚለው ሽግግር ማድረጉን ያሳያል" ሲሉ ​ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል።


ኦጎላ አክለውም፣ የሕይወት አድን የጤና እርዳታን ለማዕድን ማውጫ ስምምነቶች እንደ መደራደሪያ መጠቀም ከባድ የስነ-ምግባር ጥያቄዎችን ያስነሳል ሲሉ አስጠንቅቀዋል።


​"ማዕድናትን በተመለከተ በሰው ሕይወት መደራደር አይቻልም። መድኃኒት ሕዝብን መፈወስ እንጂ ለስምምነት መሣርያ መሆን የለበትም" ብለዋል፡፡


​ ተንታኙ አፍሪካ በተበታተነ አካሄድ ውስጥ መሆኗ የድርድር አቅሟን እንደሚያዳክም በመግለጽ "አፍሪካ አንድ ሆና መደራደር አለባት፤ በተበታተነ መልኩ ስንነጋገር ድምጻችን አይሰማም። በአንድነት ስንነጋገር ግን ዓለምን የሚያንቀሳቅስ ኃይል ይኖረናል።" ሲሉ አሳስበዋል፡፡

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X
አዳዲስ ዜናዎች
0