ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ 13,778 ጊጋ ዋት ሰዓት ኃይል በማመንጨት የዕቅዱን 95.7% አሳክቷል - የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል

ሰብስክራይብ
ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ 13,778 ጊጋ ዋት ሰዓት ኃይል በማመንጨት የዕቅዱን 95.7% አሳክቷል - የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል

ግድቡ በ2018 የበጀት ዓመት ዘጠኝ ወራት ውስጥ 13,778 ጊጋ ዋት ሰዓት የኤሌክትሪክ ኃይል በማመንጨት "የኢትዮጵያን የብርሃን ጉዞ እየመራ" መሆኑን ነው ተቋሙ የገለጸው፡፡

ይህ ስኬት በአኃዝ ሲታይ፦

የዘንድሮው የማመንጨት አቅም ካለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር የ122% ታላቅ ብልጫ አሳይቷል። (ባለፈው ዓመት 6 ሺህ 213 ጊጋ ዋት ሰዓት ተመርቶ ነበር)።

በአሁኑ ወቅት በአጠቃላይ እንደ ሀገር ከመነጨው የኤሌክትሪክ ኃይል ውስጥ ታላቁ የኢትዮጵያ የሕዳሴ ግድብ ብቻውን 51 በመቶ ድርሻ አለው።

ለዚህ ከፍተኛ ስኬት ዋነኛው ምክንያት ወደ ሥራ የገቡ ተርባይኖች ቁጥር መጨመር ነው።

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X
አዳዲስ ዜናዎች
0