ዚምባብዌ ብቸኛ የአፍሪካ እጩ በመሆን የተባበሩት መንግሥታት የፀጥታው ምክር ቤት መቀመጫን ለማግኘት ተቃርባለች - የመንግሥት ሚዲያ

ሰብስክራይብ

ዚምባብዌ ብቸኛ የአፍሪካ እጩ በመሆን የተባበሩት መንግሥታት የፀጥታው ምክር ቤት መቀመጫን ለማግኘት ተቃርባለች - የመንግሥት ሚዲያ

​ ዚምባብዌ እ.ኤ.አ ከ2027–2028  የሚቆየውን የተባበሩት መንግስታት የጸጥታው ምክር ቤት ጊዜያዊ መቀመጫ የአፍሪካ ሕብረት ብቸኛ እጩ እንደመሆኗ የማሸነፍ ሙሉ እምነት እንዳላት የሀገሪቱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አሞን ሙርዊራ አስታወቁ።

​ ሀገሪቱ ከአፍሪካ ሕብረት፣ ከደቡባዊ አፍሪካ ልማት ማኅበረሰብ፣ ከፓሲፊክ፣ ከመካከለኛው እስያ፣ ከካሪቢያን እና ከላቲን አሜሪካ ሀገራት ድጋፍ አግኝታለች።

​ ምርጫው በጎርጎሮሳዊያኑ ሰኔ 3 ቀን የሚካሄድ ሲሆን፣ የሀራሬ መንግሥት አሁን ላይ ተጨማሪ ድጋፍ ለማግኘት ከምስራቅ እና ምዕራብ አውሮፓ አጋሮች ጋር በመነጋገር ላይ ይገኛል።

ቪዲዮው  የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሙርዊራ ለዚምባብዌ በፀጥታው ምክር ቤት ጊዜያዊ መቀመጫ የማግኘት ዘመቻ ድጋፍ ለማሰባሰብ ሮማኒያ መድረሳቸውን ያሳያል፡፡

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0