ኡጋንዳ እስከ 2030 ድረስ የመንግሥት የትራንስፖርት ዘርፍን ሙሉ በሙሉ በኤሌክትሪክ ለማድረግ ማቀዷን የሀገሪቱ የነዳጅ ኮርፖሬሽን አስታወቀ

ሰብስክራይብ
ኡጋንዳ እስከ 2030 ድረስ የመንግሥት የትራንስፖርት ዘርፍን ሙሉ በሙሉ በኤሌክትሪክ ለማድረግ ማቀዷን የሀገሪቱ የነዳጅ ኮርፖሬሽን አስታወቀ

​ ሀገሪቱ በየዓመቱ የምታወጣውን የ2 ቢሊዮን ዶላር የነዳጅ ማስገቢያ ወጪ ለመቀነስ እና የአየር ብክለትን ለመከላከል በማለም፣ በአራት ዓመት ጊዜ ውስጥ ሁሉንም የህዝብ ትራንስፖርት አገልግሎቶች፣ አውቶቡሶችን እና የሞተር ሳይክል ታክሲዎችን ጨም ወደ ኤሌክትሪክ ኃይል ለመቀየር ግብ አስቀምጣለች።

​በአሁኑ ወቅት ከሀገሪቱ ሞተር ሳይክሎች ውስጥ ከ1% በታች የሚሆኑት ብቻ በኤሌክትሪክ የሚሰሩ ሲሆን፣ ጥቂት የኤሌክትሪክ አውቶቡሶችም በሙከራ ደረጃ አገልግሎት እየሰጡ ይገኛሉ።

የመንግሥት የኢ-ሞቢሊቲ ስትራቴጂ የሚከተሉትን ያካትታል፦

በአገር ውስጥ የሚገጣጠሙ ተሽከርካሪዎች የሀገር ውስጥ ግብዓት ድርሻን ከ20-30 በመቶ ወደ 65 በመቶ በ2030 ማድረስ፤

​ 3,500 የህዝብ መሙያ ጣቢያዎችን (በየ50 ኪ.ሜ አንድ ጣቢያ በመላ ሀገሪቱ) መትከል፤

በዓመት 10 ሺህ ተሽከርካሪዎችን የመገጣጠም አቅም ባላው የመንግሥት ኩባንያ 'ኪራ ሞተርስ ኮርፖሬሽን' አማካኝነት ስራውን ማፋጠን።

​ይህ የሽግግር ሂደት 1.7 ቢሊዮን ዶላር ወጪ እንደሚጠይቅ የተገመተ ሲሆን፣ ከዚህ ውስጥ 800 ሚሊዮን ዶላር ቀድሞውኑ ተገኝቷል።

በካምፓላ የተጀመረው የ'ኢ-አውቶቡስ ኤክስፕረስ የሙከራ ፕሮጀክት ይፋዊ ማስጀመሪያ

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X
አዳዲስ ዜናዎች
0