ኢትዮጵያ ከ330 ሚሊዮን ኩንታል በላይ ስንዴ በማምረት ከአፍሪካ አንደኛ ናት - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ

ሰብስክራይብ
ኢትዮጵያ ከ330 ሚሊዮን ኩንታል በላይ ስንዴ በማምረት ከአፍሪካ አንደኛ ናት - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ

ጠቅላይ ሚኒስትሩ፣ በዘንድሮው የምርት ዘመን ብቻ በክረምት 4.4 ሚሊዮን ሄክታር እንዲሁም በበጋ መስኖ 3.8 ሚሊዮን ሄክታር በድምሩ ከ8 ሚሊዮን ሄክታር በላይ መሬት በስንዴ መልማቱን፣ በኦሮሚያ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን ሱልልታ ወረዳ የስንዴ ማሳን በጎበኙበት ወቅት ተናግረዋል።


“አምናና ዘንድሮን እንኳን ብናስተያይ ወደ 950 ሺህ ገደማ ሄክታር ጭማሪ አለው። ባለፈው ዓመት ክረምትና በጋ 280 ሚሊዮን ሄክታር (ኩንታል) ገደማ ነበር ያመረት ነው። በዚህኛው ዓመት ደግሞ 331 ሚሊዮን ኩንታል ነው የምናመርተው። ይህም የሚያሳየው የ50 ሚሊዮን ኩንታል ልዩነት በአንድ ዓመት አመጣን ማለት ነው።" ብለዋል፡፡


ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X
አዳዲስ ዜናዎች
0