"አፍሪካ ባጋጠማት ከፍተኛ የብድር ጫና ምክንያት ከባድ ምጣኔ ሀብታዊና ልማታዊ ዋጋ እየከፈለች ነው" - የተባበሩት መንግሥታት የአፍሪካ ኢኮኖሚ ኮሚሽን
15:34 06.05.2026 (የተሻሻለ: 15:44 06.05.2026)
© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
"አፍሪካ ባጋጠማት ከፍተኛ የብድር ጫና ምክንያት ከባድ ምጣኔ ሀብታዊና ልማታዊ ዋጋ እየከፈለች ነው" - የተባበሩት መንግሥታት የአፍሪካ ኢኮኖሚ ኮሚሽን
የአኅጉሪቱ አጠቃላይ የውጭ ብድር መጠን 1.2 ትሪሊዮን የአሜሪካ ዶላር መድረሱን የኮሚሽኑ ዋና ጸሐፊ ክላቨር ጋቴቴ፣ በአዲስ አበባ መካሄድ በጀመረው ሁለተኛው የአፍሪካ ሉዓላዊ ፋይናንስ ጉባኤ ላይ ተናግረዋል፡፡
ዋና ጸሐፊው በብድር ጫናው ምክንያት የአፍሪካ ሀገራት ከሚሰበስቡት ገቢ አንድ አራተኛውን ለብድር ለማዋል መገደዳቸውን በመግለጽ፣ አሁናዊ ዓለምአቀፋዊ ክስተቶች ሁኔታውን የበለጠ እንዳባባሱት ጠቁመዋል፡፡
በመሆኑም ተቋማቸው፣ አፍሪካ በዓለም አቀፍ ደረጃ በወጉ ልትመዝን የምትችልባቸው መስፈርቶች እንዲዘጋጁ ከመጠየቅ ባሻገር አኅጉራዊ የምዘና ተቋምን ለማቋቋም የተጀመሩ ጥረቶችን እንደሚደግፍ አስታውቀዋል።
የኢትዮጵያ የገንዘብ ሚኒስትር ዴኤታ ሰመሪታ ሰዋሰው በበኩላቸው፣ አፍሪካ ስልታዊ በሆኑ ዓለም አቀፍ የብድር መመዘኛ መስፈርቶች ምክንያት ለከፋ የብድር ጫና፣ ለውጭ ምንዛሬ እጦት እና ለምጣኔ ሀብታዊ ቀውስ መዳረጓን ገልጸዋል።
የአፍሪካ ሀገራት ፍትሐዊ የብድር ምዘና እንዲኖር እና የጋራ ድምጻቸውን እንዲያሰሙ ጥሪ መቅረቡን የስፑትኒክ አፍሪካ ጋዜጠኛ ዘግቧል፡፡
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X