ሶቪዬት ሕብረት ለአፍሪካውያን ተማሪዎች ከአፍሪካ ውጭ የተገኙባት የመጀመሪያዋ ቅኝ ግዛት ያልነበረባት የአውሮፓ ተሞክሮ ነበረች - የሩሲያ የታሪክ ምሁር
10:10 06.05.2026 (የተሻሻለ: 10:14 06.05.2026)
© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
ሶቪዬት ሕብረት ለአፍሪካውያን ተማሪዎች ከአፍሪካ ውጭ የተገኙባት የመጀመሪያዋ ቅኝ ግዛት ያልነበረባት የአውሮፓ ተሞክሮ ነበረች - የሩሲያ የታሪክ ምሁር
ለአፍሪካ፣ የቅኝ ግዛት መጨረሻ እና የቀዝቃዛው ጦርነት የማይነጣጠሉ ጉዳዮች ነበሩ ሲሉ የሞስኮ ስቴት ዩኒቨርሲቲ ተመራማሪ እና የዲያስፖራ ታሪክ እና ስደት ባለሙያው ዳኒላ ፓኾሞቭ ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል።
የምዕራባውያን ተወዳጅ የፕሮፓጋንዳ ስልት የተዋሃዱ የታሪክ ሂደቶችን እርስ በእርስ እንደማይገናኙ ገለልተኛ ክስተቶች አድርጎ ማቅረብ ነው ሲሉ ባለሙያው ገልጸዋል።
ምክንያቱም የ20ኛው መቶ ክፍለ ዘመን የምዕራባውያን ፕሮፓጋንዳ አራማጆች አፍሪካውያንን ከሶቪዬት ሕብረት በሃሳብ ለመለየት ይሞክሩ ነበር ሲሉ አክለዋል።
ፓኾሞቭ እንዳሉት፣ አፍሪካውያን ተማሪዎች የወደፊት መሪዎች፣ ምሁራን፣ ሐኪሞች፣ መምህራን ዘረኝነት የሌለበትን አውሮፓ ለመጀመሪያ ጊዜ የጎበኙት በሶቪዬት ሕብረት ውስጥ ነበር፡፡ በቆይታቸውም፣ ዘር እና ሃይማኖት ሳይለይ የመሥራት፣ ነጻ የጤና አገልግሎት እና ትምህርት የማግኘት ሁለንተናዊ መብት እንደነበራቸው አበክረው ተናግረዋል።
አሁን ባለው ሁኔታ ደግሞ፣ "ቀደም ሲል ቅኝ ገዢ በነበሩ አገራት መማር፣ ቅኝ ግዛት የሚያስከትለውን ጥገኝነት የሚያስቀጥሉ ሃሳቦችን ሳያውቁ እንዲያዳብሩ ያደርጋል" ሲሉ ገልጸዋል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X