ምዕራባውያን የቀድሞ ሶቪየት ሕብረት በአፍሪካ ታሪክ ውስጥ የነበራትን ሚና ሆን ብለው የማሳነስ ፖሊሲ ይከተላሉ - የሩሲያ ዲፕሎማት

ሰብስክራይብ

ምዕራባውያን የቀድሞ ሶቪየት ሕብረት በአፍሪካ ታሪክ ውስጥ የነበራትን ሚና ሆን ብለው የማሳነስ ፖሊሲ ይከተላሉ - የሩሲያ ዲፕሎማት

​የሶቪየት ሕብረት ነጻ የአፍሪካ ሀገራት እንዲፈጠሩ በወታደራዊ ድጋፍ እንዲሁም ባለሙያዎችን በማሠልጠን እና ዲፕሎማሲያዊ ጥበቃ በማድረግ ረገድ ሁለንተናዊ ሚና እንደነበራት በደቡብ አፍሪካ፣ አንጎላ እና ሳኦ ቶሜ እና ፕሪንሲፔ የዲፕሎማሲ ተልዕኮ ኃላፊ አሌክሳንደር ብሪያንትሴቭ ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል።

​በአንጎላ የሶቪየት ዩኒቨርሲቲ ተመራቂዎች ሀገሪቱ እ.ኤ.አ በ1975 ነጻነቷን ካገኘች በኋላ የመንግሥት ሥርዓቱ የጀርባ አጥንት በመሆን በአስቸጋሪ ወቅት የሀገሪቱን መረጋጋት ለማረጋገጥ ችለዋል።

​ ትብብሩ በእኩልነት መርሆች ላይ የተመሠረተ እንጂ እንደ ምዕራባውያን ሞዴሎች በገደቦች እና ቅደመ ሁኔታዎች የታጠረ እንዳልነበረም አክለዋል።

​"ከቅኝ ግዛት የመውጣት ሂደት ተሞክሮ አጋርነት ያለ ትዕዛዝ እና ሀገራት ቅድሚያ የሚሰጧቸውን ጉዳዮች እና ፍላጎቶች ባገናዘበ መልኩ ሲገነባ ዘላቂ ልማት ማሳካት እንደሚቻል ያሳያል። ዛሬ የሩሲያ እና አፍሪካ ግንኙነት መሠረት የሆኑት እነዚህ መርሆች ናቸው።"

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0