ሞስኮ በ2026 የአፍሪካ ትልልቅ የንግድ አጋሮቿን ይፋ አደረገች
በሞስኮ የወጪ ንግድ ማዕከል መረጃ መሠረት፤ እ.ኤ.አ በ2026 የመጀመሪያዎቹ ሦስት ወራት ሞስኮ መቀመጫቸውን ያደረጉ ኩባንያዎች ወደ አፍሪካ ሀገራት የላኩት ምርት ከቀዳሚው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር በ52 እጥፍ አድጓል።
ዋና ዋና መዳረሻዎች፦
አልጄሪያ - በአብዛኛው የምግብ ምርት ከአጠቃላይ የላኪዎች ድርሻ 89 በመቶውን ይዛለች።
ናይጄሪያ - በኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ፣ በቴሌኮሙኒኬሽን እና በኮምፒውተር ምርቶች በመታገዝ ሌላዋ ዋና የገበያ መዳረሻ ሆናለች።
እ.ኤ.አ በ2025 ድጋፍ የተደረገላቸው የውጪ ንግድ ምርቶች ከ29 ሚሊዮን ዶላር (2.2 ቢሊዮን ሩብል) በላይ በልጠው ከዓመት እስከ ዓመት ከ37 በመቶ በላይ እድገት ታይቷል። ኤሌክትሮኒክስ እና የኤሌክትሪክ ዕቃዎች ከአጠቃላዩ ምርት ውስጥ ወደ 60 በመቶ የሚጠጋውን ድርሻ ይዘዋል።
በሞስኮ የውጭ ንግድ ማዕከል የተመቻቹ ተጠቃሽ የወጪ ንግድ ፕሮጀክቶች፦
ለዘላቂ እርሻ የሚውሉ ንጥረ-ነገሮች፣
ለከብቶች ጤና የሚውሉ ዘመናዊ ሴንሰሮች (ደቡብ አፍሪካ)፣
ከነርቭ ጋር የሚገናኙ ሰው ሠራሽ እጅና እግር (ሱዳን)፣
ከምግብ ጋር የሚወሰዱ ተጨማሪ ግብዓቶች (ግብፅ)።
ምሥል ከሞስኮ የወጪ ንግድ ማዕከል
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X