አፍሪካ ለሕዝቦቿ ጥቅም 'የራሷን ታሪክ በራሷ መተረክ' አለባት - የአፍሪካ አርታዒዎች መድረክ ፕሬዝዳንት
18:50 05.05.2026 (የተሻሻለ: 18:54 05.05.2026)
© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
አፍሪካ ለሕዝቦቿ ጥቅም 'የራሷን ታሪክ በራሷ መተረክ' አለባት - የአፍሪካ አርታዒዎች መድረክ ፕሬዝዳንት
አፍሪካውያን አሁን ከመቼውም ግዜ በላይ ህይወታቸውን የሚያሻሽሉ ውሳኔዎችን ለመወሰን የጠራ ጋዜጠኝነት እንደሚያስፈልጋቸው የአፍሪካ ሚዲያ ኮንቬንሽን አስተባባሪ ኮሚቴ ሰብሳቢ እና የአፍሪካ አርታዒዎች መድረክ ፕሬዝዳንት ቸርችል ኦቲኖ ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል።
"ዛሬ በወሳኝ ወቅት ላይ እንገኛለን። እስካሁን ያለፍንበትን ግዜ በመገምገም እና ከተሞክሯችን በመነሳት መዋቅሮቻችንን በማጠናከር የሚዲያውን ዘርፍ ለማነቃቃት እየሠራን ነው" ብለዋል።
አሁን ላይ ዜጎች ሃሳባቸውን እና አስተያየታቸውን ከበፊቱ በበለጠ ሁኔታ በስፋት ማሰራጨት መቻላቸው "መልካም ነገር ነው" ሲሉም ኦቲኖ ገልጸዋል።
"ይሁን እንጂ ይህ በተለይም ከመረጃዎች ትክክለኛነት ወይም ከመረጃ መዛባት ጋር ተያይዞ ትልቅ ተግዳሮቶችን ይዞ መጥቷል። እነዚህን ችግሮች መፍታት አለብን" ብለዋል።
በሉሳካ ይጸድቃል ተብሎ የሚጠበቀው የአፍሪካ ሚዲያ ኮንቬንሽን በአፍሪካ ኅብረት የሚዲያ እና የመረጃ ፖሊሲዎች ላይ ምን አይነት ተፅዕኖ እንደሚኖረው ለማወቅ ቪዲዮውን ይመልከቱ።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X