የናይጄሪያ የመፈንቅለ መንግሥት ተጠርጣሪዎች በቦላ ቲኑቡ ላይ ስለተሸረበው ሴራ እንደሚያወቁ የገለጹበት የቪዲዮ ማስረጃ በፍርድ ቤት ቀረበ
17:50 05.05.2026 (የተሻሻለ: 17:54 05.05.2026)
© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
የናይጄሪያ የመፈንቅለ መንግሥት ተጠርጣሪዎች በቦላ ቲኑቡ ላይ ስለተሸረበው ሴራ እንደሚያወቁ የገለጹበት የቪዲዮ ማስረጃ በፍርድ ቤት ቀረበ
አቃቤ ሕግ ባቀረበው የቪዲዮ ማስረጃ ጡረተኛው የባሕር ኃይል ካፒቴን ኤራስመስ ቪክቶር እና የፖሊስ ኢንስፔክተር አህመድ ኢብራሂም፤ የፕሬዚዳንት ቦላ ቲኑቡን አስተዳደር ለመጣል የታቀደ መፈንቅለ መንግሥት እንደነበር እንደሚያውቁ አምነዋል።
🟠 በክሱ የተካተቱት ሌላኛው ተከሳሽ ጡረተኛው ሜጀር ጄኔራል መሐመድ ኢብራሂም ጋና፤ ምንም ዓይነት ሴራ እንደማያውቁ እና መልዕክቶችን ያስተላለፉት ይዘቱን ሳይረዱ መሆኑን በመግለጽ ተሳትፎ እንደሌላቸው በመካድ ተከራክረዋል።
🟠 የቀድሞ የባዬልሳ ግዛት አስተዳዳሪ ቲምፕሬ ሲልቫ በክሱ ውስጥ ስማቸው የተጠቀሰ ቢሆንም እሳካሁን በቁጥጥር ስር እንዳልዋሉ ተገልጿል።
🟠 የፍርድ ሂደቱ ሲቀጥል ተከሳሾቹ ቃላቸውን በፈቃደኝነት መስጠታቸውን ለማጣራት የተለየ ችሎት ይካሄዳል።
🟠 ስድስቱ የተከሰሱ ግለሰቦች ጥፋተኛ እንዳልሆኑ ገልጸዋል።
ቪዲዮው ተከሳሾቹ በአቡጃ የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ሲቀርቡ ያሳያል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X