የተመድ የሰብዓዊ እርዳታ አስተባባሪ ካትሪን ሶዚ እንደገለጹት፤ ድጋፉ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ተጋላጭ ክፍሎች ተጠቃሚ ያደርጋል፦
17:17 05.05.2026 (የተሻሻለ: 18:44 05.05.2026)
© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት በግጭትና በአየር ንብረት ለተጎዳችው ሞዛምቢክ ወደ 98 ሚሊዮን ዶላር የሚጠጋ አስቸኳይ እርዳታ ለቀቀ
የተመድ የሰብዓዊ እርዳታ አስተባባሪ ካትሪን ሶዚ እንደገለጹት፤ ድጋፉ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ተጋላጭ ክፍሎች ተጠቃሚ ያደርጋል፦
▪ ሰብልና የገቢ ምንጫቸውን ላጡ ቤተሰቦች ምግብ፣
▪ በጎርፍ በተጥለቀለቁ ወይም በተበከሉ አካባቢዎች ደህንነቱ የተጠበቀ የመጠጥ ውሃ፣
▪ ከመሠረታዊ አገልግሎቶች ለተቋረጡ ወገኖች የጤና እንክብካቤ፣
▪ ለአስቸኳይ ጊዜ መጠለያ፣
▪ ለጥቃት ተጋላጭ ለሆኑ ሴቶች፣ ህፃናትና ሌሎች ወገኖች ጥበቃ።
ሞዛምቢክ በሰሜናዊቷ ካቦ ደልጋዶ ግዛት በሚካሄድ ግጭት እና በማዕከላዊና ደቡባዊ ክልሎች በሚከሰቱ ከባድ የጎርፍና አውሎ ንፋስ አደጋዎች እየተፈተነች ትገኛለች።
ይህ የገንዘብ ድጋፍ የተመድ እና የሞዛምቢክ መንግሥት በ534 ሚሊዮን ዶላር 1.7 ሚሊዮን ሰዎችን ለመድረስ በጋራ ያረቀቁትን የ2026 የሰብዓዊ ፍላጎትና ምላሽ ዕቅድ ይደግፋል።
ቪዲዮው እ.ኤ.አ በ2024 መጨረሻ በሀገሪቱ የደረሰውን የቺዶ አውሎ ንፋስ ጥፋት ያሳያል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X