የኬንያ ፕሬዚዳንት በታንጋ ማጣሪያ ዙሪያ ባደረጉት ንግግር በዳሬሰላም ተገሠፁ
ዊሊያም ሩቶ በታንጋ የነዳጅ ማጣሪያ ለመገንባት መታቀዱን ቀድመው ይፋ ማድረጋቸውን ያልወደዱት የታንዛኒያ ፕሬዚዳንት ሳሚያ ሱሉሁ ሀሰን፤ እንዴት ያለኔ መንግሥት እውቅና ይገለጻል ብለው ባልተጠበቀ መንገድ ተቃውሟቸውን አሰምተዋል።
"ውስጥ ስንነጋገር ሩቶን አጥብቄ ጠይቄዋለሁ። በራስህ ስለታንጋ የነዳጅ ማጣሪያ ይፋ አድርገሃል - ለምን ቅድሚያ እኔ አላወቅኩም ነበር? ብዬዋለሁ። ለምን በራሱ ይፋ እንዳደረገው ያስረዳል" ሲሉ በስዋሂሊኛ ተናግረዋል።
ሩቶ የነዳጅ ማጣሪያ ፋብሪካው በአሊኮ ዳንጎቴ የሚደገፍ እና በርካታ ሀገራትን የሚያካትት ክልላዊ ፕሮጀክት እንደሆነ ቀደም ሲል ይፋ አድርገው ነበር።
ሩቶ የተነሳባቸውን ጥያቄ ተከትሎ ውጥረቱን ለማርገብ በሞከሩበት መልሳቸው፤ “በታንጋ የነዳጅ ማጣሪያ ስለመገንባት ይፋ መደረጉ በጣም እንዳስቆጣቸው ተነግሮኛል…ባውቅ ኖሮ የነዳጅ ማጣሪያው በሞምባሳ እንደሚገነባ ይፋ አደርግ ነበር” ብለዋል።
ሁለቱ ሀገራት በመጨረሻም የንግድ ትብብራቸውን ለማሻሻል እና እንቅፋቶችን ለመቀነስ የመግባቢያ ስምምነት ተፈራርመዋል።
በእንግሊዘኛ ያንብቡ
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X