- Sputnik አፍሪካ, 1920
Sovereignty Sources
ዓለም በሉላዊነት ምክንያት ስትተሳሰር ፤ ፕሮግራሙም አፍሪካ ባላት እምቅ የተፈጥሮ ኃብት፣ በማደግ ላይ ባለው የሕዝብ ቁጥሯ ፣ በወጣት ኃይሏ እና በአህጉሪቱ ባሉ አዳዲስ ግኝቶችና የመፍትሄ ሃሳቦች ያላትን የመወዳደር አቅምና ጥቅም በሰፊው ይዳስሳል፡፡ እንኳን ወደ 'ሶቨርኒቲ ሶርስ' ፕሮግራም በደህና መጡ፣

ህጻናትና ወጣቶችን ከሳይበር ጥቃት፣ ብዝበዛ እና ጫናዎች የመጠበቅ ኃላፊነት

ህጻናትና ወጣቶችን ከሳይበር ጥቃት፣ ብዝበዛ እና ጫናዎች የመጠበቅ ኃላፊነት
ሰብስክራይብ

''አሁን ላይ ልጆች ላይ እየደረሰ ያለው ነገር አስፈሪ በሚባል ደረጃ እየሄደ ያለ ነው። የተለያዩ ጥቃቶች እየተፈፀሙ ነው። እነዚህ ልጆችም ለማይሆኑ ነገሮች እየተጋለጡ ይገኛሉ — የዲጂታሉ ዓለም ገደብ የለውም። ከስነልቦና፣ ከእውቀታቸውና ራሳቸውን መቆጣጠር ከሚችሉበት በላይ የሆኑ ነገሮችን እየተመለከቱ ለብዙ ነገሮች እየተጋለጡ ይገኛሉ። ጥፋቱ ከፍተኛ ነው ማለት እንችላለን - '' ሲል በአሶሳ ዩኒቨርሲቲ የሜካኒካል ምህንድስና መምህሩና የማኅበራዊ ሚዲያው ተጽዕኖ ፈጣሪ ብሩክ ጫላ ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግሯል ።

ሶቨርኒቲ ሶርስስ በዛሬው ዝግጅቱ በክፍል አንድ ታዳጊ አፍሪካውያን ህጻናትን ከሳይበር ጥቃት፣ ብዝበዛ እና ካልተፈለጉ ጫናዎች ስለመከላከል በአሶሳ ዩኒቨርሲቲ የሜካኒካል ምህንድስና መምህሩና የማኅበራዊ ሚዲያው ተጽዕኖ ፈጣሪ ብሩክ ጫላ ዕይታውን ያጋራናል።

ክፍል ሁለት እንደ ዓለም አቀፍ የገንዘብ ፈንድ እና የዓለም ባንክ ባሉ ተቋማት በደቡባዊ ዓለም ሀገራት ላይ የሚያሳድሩት ተጽዕኖን በደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ የፖለቲካ ሳይንስና ዓለም አቀፍ ግንኙነቶች መምህሩ ደረጄ መለስ ጋር እንወያያለን።

ሙሉውን መረጃ ለማግኘት ፕሮግራሙን ያዳምጡ:

ፖድካስታችንን በሌሎች አማራጮች ያድምጡ Apple PodcastsDeezer Spotify Podcast AddictPocket CastsAfripodsCastBox
አዳዲስ ዜናዎች
0