አፍሪካ በዘረምል ቴክኖሎጂ ራሷን ለመምራት የሚያስችላትን ስልታዊ አማካሪ ቡድን አቋቋመች

ሰብስክራይብ

አፍሪካ በዘረምል ቴክኖሎጂ ራሷን ለመምራት የሚያስችላትን ስልታዊ አማካሪ ቡድን አቋቋመች

አፍሪካ ሲዲሲ በአኅጉሪቱ የዘረመል አስተዳደር ገለልተኛ ቴክኒካዊ መመሪያ የሚሰጥ አዲስ አማካሪ ቡድን መቋቋሙን አስታውቋል።

የአማካሪ ቡድኑ ዋና ዋና ተግባራት፦

የበሽታዎች ክትትል፦ እንደ ኤምፖክስ፣ ኮሌራ፣ ወባና ወረርሽኝ ያሉ በሽታዎችን ለመከታተልና ምላሽ ለመስጠት ድጋፍ ያደርጋል።

የቴክኖሎጂ ሽግግር፦ በአኅጉሪቱ የሕክምና ግብዓቶች ማምረቻ እንዲስፋፋና የቴክኖሎጂ ሽግግር እንዲኖር ምክር ሀሳብ ያቀርባል።

ፍትሐዊ ተጠቃሚነት፦ አፍሪካውያን በዘረመል የምርምር ውጤቶች እኩል ተጠቃሚ እንዲሆኑና የመረጃ አስተዳደር እንዲሁም ሥነ-ምግባራዊ ጉዳዮች እንዲጠበቁ ይሠራል።

⬇ ቀደም ሲል አፍሪካውያን ባለሙያዎች በዚህ ርዕሰ ጉዳይ ላይ ለስፑትኒክ አፍሪካ ያጋሩት ሀሳብ ምን ይመስላል?

ደቡብ አፍሪካዊው ፕሮፌሰር ኬሊ ቺባሌ፤ የአፍሪካ የተለያዩ የዘረመል ዓይነቶች የዓለም አቀፍ መድኃኒቶችን ውጤታማነት እና ደህንነት ለማሻሻል ቁልፍ መሆናቸውን አጽንዖት ሰጥተዋል። ዶክተር ሴሳር ፎርቴስ-ሊማ በበኩላቸው፤ በዘረመል ምርምር ዙሪያ ሥር የሰደዱ አድልዎችን መፍታት ወሳኝ እንደሆነ አክለዋል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ፤ ፕሮፌሰር ኤሚሌ ሩጋሚካ ቺሙሳ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ሰፊ የዘረመል ውሂቦችን እንዴት እየፈታ እንደሆነ በመጥቀስ፤ አፍሪካውያን ሳይንቲስቶችን በዚህ የዝምታ ሳይንሳዊ አብዮት ግንባር ቀደም እንዲሆኑ እያደረገ መሆኑን ገልጸዋል። ፕሮፌሰር ኮሌት ዳንዳራ እና ዶክተር ግላዲስ ዙግዋይ ኢብራሂም ይህንን አመለካከት በማጠናከር፤ ስለ ሰው ልጅ ባዮሎጂ እውነተኛ ግንዛቤ ማግኘት የሚቻለው ከአፍሪካ የዲኤንኤ ጥናት ሲጀመር እንደሆነ አስምረውበታል።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0