ደቡብ አፍሪካ በአቪዬሽን ደህንነት በዓለም አቀፍ ደረጃ 8ኛ ደረጃን ያዘች
የደቡብ አፍሪካ ሲቪል አቪዬሽን ባለሥልጣን ባወጣው ሪፖርት መሠረት፤ ሀገሪቱ ዓለም አቀፍ የሲቪል አቪዬሽን ድርጅት ባካሄደው ኦዲት 95.12 በመቶ የመጀመሪያ ደረጃ ውጤት አግኝታለች።
የትራንስፖርት ሚኒስትሯ ባርባራ ክሪሲ፤ "ውጤቱ የሥርዓታችንን ጥንካሬ እና የሰማያችንን ደህንነት ለማረጋገጥ የተደረገውን የጋራ ጥረት ያንጸባርቃል" ብለዋል።
ይህ ጠንካራ ደረጃ የሀገሪቱ የቁጥጥር ሥርዓት ከዓለም አቀፍ ምርጥ ተሞክሮዎች ጋር የተጣጣመ መሆኑን የሚያሳይ እና ቀጣይነት ያለው ዓለም አቀፍ ትስስር፣ የገበያ ተደራሽነት እና ለአቪዬሽን ዘርፉ የረጅም ጊዜ ዕድገት ድጋፍ የሚሰጥ ነው ተብሏል።
የባለሥልጣኑ የሲቪል አቪዬሽን ዳይሬክተር ፖፒ ኮዛ፤ "ይህ አስደናቂ ውጤት ደቡብ አፍሪካ በንግድ አየር መንገድ ዘርፍ ላለፉት አራት አስርት ዓመታት ያስመዘገበችው የዜሮ ሞት አደጋ መጠን ተጨማሪ ማረጋገጫ ነው" ሲሉ አፅንዖት ሰጥተዋል።
በእንግሊዘኛ ያንብቡ
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X