ቦይንግ ከሰባት ዓመታት በፊት በኢትዮጵያ በደረሰው አደጋ ዙሪያ አዲስ ክስ ቀረበበት
18:04 04.05.2026 (የተሻሻለ: 18:39 04.05.2026)

ሰብስክራይብ
ቦይንግ ከሰባት ዓመታት በፊት በኢትዮጵያ በደረሰው አደጋ ዙሪያ አዲስ ክስ ቀረበበት
መጋቢት 1 ቀን 2011 ዓ.ም ከአዲስ አበባ ወደ ናይሮቢ ሲበር በተከሰከሰው 737 ማክስ 8 አውሮፕላን ሕይወቷ ያለፈው የአሜሪካዊቷ ሳምያ ስቱሞ ቤተሰቦች፤ በቦይንግ ኩባንያ ላይ የመሰረቱት ክስ በዛሬው ዕለት በቺካጎ ፌደራል ፍርድ ቤት መታየት ይጀምራል ተብሏል።
ቦይንግ ከአደጋው ጋር በተያያዘ እስካሁን የቀረቡበትን 155 የፍትሐ ብሔር ክሶች በስምምነት ዘግቷል።
የስቱሞ የፍርድ ጉዳይ የአውሮፕላን አምራቹን የወንጀል ተጠያቂነት ማረጋገጥ ሳይሆን ለተጎጂ ዘመዶች የሚከፈለውን የገንዘብ ካሳ የመወሰን ዓላማ እንዳለው ተነግሯል።
በመጨረሻ ሰዓት ስምምነት ላይ ካልተደረሰ ጉዳዩ ፍርድ ቤት ቀርቦ ሰኞ እና ማክሰኞ የሕዝብ ዳኞች (ጁሪ) ምርጫ እና ረቡዕ የመክፈቻ መከራከሪያ እንደሚካሄድ ይጠበቃል።
ባለፈው ህዳር ወር በተመሳሳይ ክስ የቺካጎ ዳኝነት ቡድን ቦይንግ ለአንድ ተበዳይ ቤተሰብ 28.45 ሚሊዮን ዶላር ካሳ እንዲከፈል መወሰኑ ይታወሳል፡፡
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X