አልጄሪያ በኒጀር የምትገነባውን የኃይል ማመንጫ ጣቢያ በ3 ወራት ውስጥ እንደምታጠናቅቅ ፕሬዚዳንት ቴቦን ገለፁ

ሰብስክራይብ

አልጄሪያ በኒጀር የምትገነባውን የኃይል ማመንጫ ጣቢያ በ3 ወራት ውስጥ እንደምታጠናቅቅ ፕሬዚዳንት ቴቦን ገለፁ

የአልጄሪያ ፕሬዚዳንት ፕሮጀክቱን "ታሪካዊ ስኬት" እና የሁለቱ ሀገራት ጠንካራ ትብብር ማሳያ ሲሉ ቀደም ሲል በሚኒስትሮች ምክር ቤት ስብሰባ ወቅት ገልጸውታል።

"ሶሊዳሪቲ" ተብሎ የተሰየመው ይህ የኃይል ማመንጫ፤ በአልጄሪያው ሶኔልጋዝ ድጋፍ የኒጀርን የኤሌክትሪክ አቅርቦት ለማረጋጋት እና የኢነርጂ ደህንነቷን ለማጠናከር ያለመ ነው።

ቴቦን በተጨማሪም ሁለቱ ሀገራት ትብብራቸውን በሃይድሮካርቦን፣ በነዳጅ ፍለጋ እና በጋራ የመገናኛ ብዙኃን አጋርነት ዙሪያ እንዲያሰፉ አቅጣጫ ሰጥተዋል።

ይህ የ40 ሜጋ ዋት ፕሮጀክት የተጀመረው የኒጀር መሪ ባለፈው የካቲት ወር በአልጄሪያ ካደረጉት ይፋዊ ጉብኝት በኋላ ነው። እያንዳንዳቸው 20 ሜጋ ዋት የማመንጨት አቅም ያላቸው ሁለት የጋዝ ተርባይኖችን ወደ ሥራ በማስገባት የኒጀርን የቤት ውስጥ እና የኢንዱስትሪ ፍላጎቶችን መደገፍ ያካትታል።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0