103 የኢትዮጵያ የገጠር ከተሞች እና መንደሮች ባለፉት ዘጠኝ ወራት ለመጀመሪያ ግዜ የኤሌክትሪክ ተጠቃሚ መሆናቸው ተገለፀ

የኤሌክትሪክ ተደራሽነት
የኤሌክትሪክ ተደራሽነት  - Sputnik አፍሪካ, 1920, 04.05.2026
ሰብስክራይብ
103 የኢትዮጵያ የገጠር ከተሞች እና መንደሮች ባለፉት ዘጠኝ ወራት ለመጀመሪያ ግዜ የኤሌክትሪክ ተጠቃሚ መሆናቸው ተገለፀ

በሦስተኛው ሩብ የበጀት ዓመት 82ቱን ከዋናው የኤሌክትሪክ መረብ፤ ቀሪዎቹን 21 የገጠር ከተሞችና መንደሮች ደግሞ በፀሐይ ኃይል አማራጭ የኃይል ተጠቃሚ ማድረጉን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት አስታውቋል።

ቁልፍ አሃዞች፦

በተጠቀሰው ግዜ 423 ሺህ 200 አዲስ ደንበኞችን የኤሌክትሪክ ኃይል ተጠቃሚ ሆነዋል፣
ከአምናው ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፀር የ18.6 በመቶ ብልጫ አለው፣
አጠቃላይ የኤሌክትሪክ አገልግሎት ተጠቃሚዎች ቁጥር 5.64 ሚሊዮን ደርሷል፡፡


የአገልግሎቱ ዋና ሥራ አስፈፃሚ ኢንጅነር ጌቱ ገረመው፤ “በአዳዲሶቹ አካባቢዎች ከጤና እና ማኅበራዊ ተቋማት በተጨማሪ ከ31 ሺህ በላይ አባዎራዎችና እማዎራዎች የኤሌክትሪክ አገልግሎት ተጠቃሚ ሆነዋል” ማለታቸውን ጠቅሶ የመንግሥት የዜና አውታር ዘግቧል፡፡


ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X
አዳዲስ ዜናዎች
0