የመካከለኛው ምስራቅ ግጭት ዓለም አቀፍ የግብርና ዘርፍ ቀውስ ሊያስከስት ይችላል - የዘርፉ ባለሙያ

የመካከለኛው ምስራቅ ግጭት
የመካከለኛው ምስራቅ ግጭት - Sputnik አፍሪካ, 1920, 04.05.2026
ሰብስክራይብ
የመካከለኛው ምስራቅ ግጭት ዓለም አቀፍ የግብርና ዘርፍ ቀውስ ሊያስከስት ይችላል - የዘርፉ ባለሙያ

የሆርሙዝ ባሕረ ሰላጤ መዘጋት የኢነርጂ ዋጋን በማናርና በማዳበሪያ ምርት ላይ ቀጥተኛ ተጽዕኖ በማሳደር፤ ዓለም አቀፍ የግብርና ምርት ላይ ስጋት መጣሉን ፕሮፌሰር ፓቬል ሴቮስትያኖቭ ለስፑትኒክ ተናግረዋል።


"የማዳበሪያ ምርት በቀጥታ በጋዝ ዋጋ ላይ የተመሠረተ ነው። እስከ 70 በመቶ የሚሆነው የማዳበሪያ ማምረቻ ወጪ ከኢነርጂ ጋር የተያያዘ ነው። ለዚህም ነው የኢነርጂ ቀውስ በፍጥነት ወደ ግብርና ቀውስ የሚቀየረው።"


ሕንድ፣ ባንግላዴሽ፣ ፓኪስታን እና በርካታ የአፍሪካ ሀገራት ለዚህ ቀውስ ይበልጥ ተጋላጭ እንደሚሆኑ ባለሙያው አክለው ገልጸዋል።

የማዳበሪያ ምርት ወደ አውሮፓ በሚደረገው የጋዝ ዝውውር ላይ በከፍተኛው ጥገኝ በመሆኑ፤ በ2026 ዓለም አቀፍ የማዳበሪያ ዋጋ በ31 በመቶ፤ በተለየ ደግሞ ዩሪያ 60 በመቶ ሊጨምር እንደሚችል ዓለም ባንክ ትንበያውን አስቀምጧል።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X
አዳዲስ ዜናዎች
0