የሩሲያ "አፍሪካ ኮር" በማሊ አሸባሪዎችን እና ተባባሪዎቻቸውን ደመሰሰ
በቁጥጥር ስር የዋሉ ጂሃዲስቶች የፈረንሳይ እና የዩክሬን የስለላ ድርጅቶች የመፈንቅለ መንግሥት ሙከራውን በማቀድ እና በማስተባበር ረገድ ቀጥተኛ ተሳትፎ እንዳላቸው ማረጋገጣቸውን የሩሲያ ጦር የአፍሪካ ኮር አስታውቋል።
ኮሩ ተልዕኮዎቹን ከማሊ ጦር ጋር በቅርበት በመቀናጀት እንደሚያከናውን ገልጿል።
በቅርቡ የተከናወኑ ቁልፍ ዘመቻዎች፦
🟠 የአሸባሪዎች የአድፍጦ ማጥቂያ ቦታዎች ተለይተው ከ40 በላይ አክራሪዎች እና አምስት ፒክ አፕ መኪናዎች ተደምስሰዋል።
🟠 በጋኦ ክልል ሰፊ የአሸባሪዎች ዝግጅት በከባድ የአየር ድብደባ ተመቷል። ከ30 በላይ ታጣቂዎች እና 20 ተሽከርካሪዎች ወድመዋል።
🟠 የሩሲያ እና የማሊ ጥምር ጦር በባማኮ አውሮፕላን ማረፊያ፣ በካባራ እና በቲምቡክቱ አካባቢዎች የአሰሳ ሥራ በማከናወን አሸባሪዎቹን በመድፍ እና በአየር ድብደባ በትነዋል።
🟠 ሚያዝያ 24 በሜናካ ከተማ በተደረገው የጥበቃ ሥራ ምንም ዓይነት አሸባሪ ያልተገኘ ሲሆን በከተማዋም መረጋጋት ሰፍኗል።
በጋራ በተደረገው ጥረት ዋና ከተማዋ መረጋጋቷን የአፍሪካ ኮር ገልጿል። በዚህም ማሊ በባማኮ ከሚያዝያ 17 ጀምሮ ተጥሎ የነበረውን የሰዓት እላፊ ገደብ አንስታለች።
ቪዲዮዎች፦ 1) የሜናካ ቅኝት 2) የጋራ ጥቃቶች። በአፍሪካ ኮር የተቀረጹ።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X