ዳንጎቴ ለደቡባዊ አፍሪካ ቀጣና የሚውል የነዳጅ ማከፋፈያ ማዕከል በናሚቢያ ሊያቋቁም ነው

ዳንጎቴ
ዳንጎቴ  - Sputnik አፍሪካ, 1920, 03.05.2026
ሰብስክራይብ
ዳንጎቴ ለደቡባዊ አፍሪካ ቀጣና የሚውል የነዳጅ ማከፋፈያ ማዕከል በናሚቢያ ሊያቋቁም ነው

በአፍሪካ ግዙፉ ነዳጅ ማጣሪያ ከአፍሪካ ኤክስፖርት-ኢምፖርት ባንክ (አፍሪኤግዚም) ጋር በመተባበር በናሚቢያ የነዳጅ ማዕከል ለመገንባት ማቀዱን አንድ የሀገር ውስጥ ቴሌቪዥን ጣቢያ ዘግቧል። ይህም ከመካከለኛው ምስራቅ ግጭት ጋር ተያይዞ ከፋርስ ባህረ ሰላጤ በሚመጣ ነዳጅ ላይ ያለውን ጥገኝነት ለመቀነስ ያለመ ነው።

10 ቢሊዮን ዶላር የሚፈጀው ይህ ማዕከል፤ ከናይጄሪያ የሚላክ ነዳጅ የሚፈጅበትን ጊዜ ወደ 5 ቀናት ዝቅ የሚያደርግ ሲሆን በ18 ወራት ውስጥ የነዳጅ ዋጋን ከ15-20 በመቶ ይቀንሳል ተብሎ ይጠበቃል። ባንኩ ከግል ባለሀብቶች በሚገኝ ገንዘብ 550 የነዳጅ ማጓጓዣ ቦቴዎችን እየገዛ ይገኛል።

የአፍሪካ ኤክስፖርት-ኢምፖርት ባንክ ከፍተኛ ምክትል ፕሬዝዳንት ዴኒስ ዴንያን ጠቅሶ ጣቢያው እንደዘገበው፤ የነዳጅ ጫኝ መርከቦች ምርቱን ወደ ዋልቪስ ቤይ ወደብ ካደረሱ በኋላ በየብስ ትራንስፖርት አማካኝነት ለቦትስዋና፣ ዛምቢያ እና ዚምባብዌ ይሰራጫል።

በሰው ሠራሽ አስተውህሎት የበለጸገ ምሥል

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X
አዳዲስ ዜናዎች
0