የ “ሌማት ትሩፋት” በኢትዮጵያ የዓሣ ጫጩት ስርጭትን በ32.5 እጥፍ ማሳደጉ ተገለፀ
18:56 03.05.2026 (የተሻሻለ: 19:20 03.05.2026)

ሰብስክራይብ
የ “ሌማት ትሩፋት” በኢትዮጵያ የዓሣ ጫጩት ስርጭትን በ32.5 እጥፍ ማሳደጉ ተገለፀ
በሀገሪቱ ቀደም ሲል 400 ሺህ የነበረው የዓሣ ጫጩት ዓመታዊ ስርጭት በመርኃ-ግብሩ አማካኝነት ወደ 13 ሚሊዮን ከፍ ማለቱን የግብርና ሚኒስቴር አስታውቋል።
የግብርና ሚኒስትር ዴኤታ ፍቅሩ ረጋሳ (ዶ/ር)፤ ከሐይቆች ባሻገር በኩሬ ማልማት ላይ ትኩረት በመደረጉና የጫጩት ማባዣ ማዕከላትን በማጠናከር የምርት ዕድገቱ ተመዝግቧል ብለዋል።
በዚህም እንደ ቦንጋ፣ ሶማሌ ክልል፣ ሰበታ እና ሆለታ ያሉ አዳዲስ የዓሣ አምራች አካባቢዎች መፍጠር መቻሉን ገልፀዋል።
ቀደም ሲል በባልዲ ይከናወን የነበረው የጫጩት ስርጭት አሁን በዘመናዊ መኪኖች መተካቱ ጫጩቶቹ ሳይጎዱ ወደ ተፈለገው ቦታ እንዲደርሱና ምርታማነቱ በአጭር ጊዜ እንዲጨምር ማድረጉን የሀገር ውስጥ ሚዲያ ዘግቧል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X