የዓለም የፕሬስ ነፃነት ቀን፦ የአፍሪካ መሪዎች ሰለ ፕሬስ ነፃነት ምን አሉ?
18:47 03.05.2026 (የተሻሻለ: 18:54 03.05.2026)
© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
የዓለም የፕሬስ ነፃነት ቀን፦ የአፍሪካ መሪዎች ሰለ ፕሬስ ነፃነት ምን አሉ?
ዛሬ ሚያዝያ 23 የዓለም የፕሬስ ነፃነት ቀን ነው። ዕለቱ እ.ኤ.አ በ1993 የታወጀው የአፍሪካ የዊንድሆክ የፕሬስ ነፃነት አዋጅ ታስቦ የሚውልበት ነው።
የናሚቢያ ፕሬዝዳንት ኔቱምቦ ናንዲ-ንዳይትዋ፦
"በተለያዩ ቀጣናዎች የጂኦፖለቲካ ውጥረት፣ የተዛቡና ሀሰተኛ መረጃዎች መስፋፋት እንዲሁም በመገናኛ ብዙኃን ተቋማት ላይ እየበረታ የመጣ ጫና እያየን ነው። በዚህ ዐውድ የነፃ እና ተጠያቂ ፕሬስ ሚና ለሕዝብ መረጃ ከመስጠት ባለፈ እውነትን ለመጠበቅ፣ ውይይትን ለማበረታታት እና በማኅበረሰቦች መካከል ያለው እምነት እንዳይሸረሸር ለመከላከል ይበልጥ ወሳኝ ይሆናል።"
የዚምባብዌ የማስታወቂያ ሚኒስትር ዜሙ ሶዳ፦
"የፕሬስ ነፃነት መከፋፈያ መሣሪያ ሳይሆን ማኅበረሰቦችን የሚያገናኝ፣ የተለያዩ ድምፆችን የሚያጎላ እና የጋራ ሀገራዊ ታሪክን የሚገነባ ድልድይ መሆን አለበት። ይህ ነፃነት በልዩነቶቻችን ላይ በትህትና እየተከራከርን አንድ የሚያደርጉንን ነገሮች ለማክበር ይውል ዘንድ እመኛለሁ።"
የኮንጎ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ መንግሥት ቃል አቀባይ ፓትሪክ ሙያያ፦
"በዚህ ቀን ይበልጥ ነፃ፣ ተጠያቂ እና በኢኮኖሚ የበቃ እንዲሁም ሀሰተኛ መረጃዎችን የሚዋጋ በእውነትም አጋር የሆነ ፕሬስ ለመፍጠር ለምናደርገው ጥረት ያለንን ቁርጠኝነት እናድሳለን።"
የሴኔጋል ፕሬዝዳንት ባሲሩ ዲዮማዬ ፋዬ፦
"እኔ ሥልጣን የተቆናጠጡትን በሚሞግትበት ጊዜም ቢሆን፤ ፕሬስ ነፃ በሆነባት ሀገር ፕሬዚዳንት ነኝ። ዲሞክራሲ ማለት ይሄ ነው።"
ቪዲዮው በዛምቢያ የተካሄደውን የዓለም የፕሬስ ነፃነት ቀን አከባበር ያሳያል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X