ኢትዮጵያ የዓለም የንግድ ድርጅት አባል ለመሆን በምታደርገው ጥረት በነዳጅ የሚሠሩ ተሽከርካሪዎች ላይ የጣለችውን እገዳ ልታጤን እንደምትችል ገለጸች

ኢትዮጵያ
ኢትዮጵያ  - Sputnik አፍሪካ, 1920, 03.05.2026
ሰብስክራይብ
ኢትዮጵያ የዓለም የንግድ ድርጅት አባል ለመሆን በምታደርገው ጥረት በነዳጅ የሚሠሩ ተሽከርካሪዎች ላይ የጣለችውን እገዳ ልታጤን እንደምትችል ገለጸች

የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር ካሳሁን ጎፌ፤ በርጄኔቫ በተካሄደው 7ኛው የኢትዮጵያ የዓለም ንግድ ድርጅት አባልነት የሥራ ቡድን ስብሰባ ገደቡ በድጋሚ ሊታይ እንደሚችል ገልጸዋል፡፡


የኢትዮጵያ መንግሥት ድርጅቱን ለመቀላቀል በሚያደርገው ጥረት እያከናውናቸው ስለሚገኙ ሥራዎች ሲያብራሩ፤ "የአሮጌ ልብሶች ገቢ እገዳ አንስተን ከድርጅቱ መስፈርቶች ጋር በሚጣጣም መልኩ በተግባራዊ የጉምሩክ ቀረጥ ተክተነዋል። አባል ከመሆናችን በፊት በነዳጅ የሚሠሩ ተሽከርካሪዎች እና ባለሦስት እግር ተሽከርካሪዎች ላይ የጣልነውን ገደብ በተመለከተም ተመሳሳይ አካሄድ ለመከተል አስበናል" ብለዋል።


ይሁን እንጂ እገዳው መነሳቱ የነዳጅ ተሽከርካሪዎች በስፋት እንዲገቡ ይፈቀዳል ማለት እንዳልሆነ በሚኒስቴሩ የዓለም አቀፍ ንግድ ተደራዳሪ ታገሰ ሙለታ ነግረውኛል ሲል የሀገር ውስጥ ሚዲያ ዘግቧል።

የአካባቢ ጥበቃን ከግምት ውስጥ ያስገቡ ከፍተኛ የታክስ ተመኖችን በመጣል እና በመሠል እርምጃዎች የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች እንዳይገቡ መከላከል እንደሚቻል ገልፀዋል።

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X
አዳዲስ ዜናዎች
0