“ማምረት ሉዓላዊነትን ያጎናፅፋል፤ አለማምረት ደግሞ ታሪክን ያጎድፋል” - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ
17:33 03.05.2026 (የተሻሻለ: 18:17 03.05.2026)

ሰብስክራይብ
“ማምረት ሉዓላዊነትን ያጎናፅፋል፤ አለማምረት ደግሞ ታሪክን ያጎድፋል” - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ
የሀገሪቱ ርዕሰ መስተዳደር አራተኛውን የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ ኤክስፖ መርቀው ከፍተዋል።
“በዘንድሮው ‘ኢትዮጵያ ታምርት’ ኤክስፖ ላይ የሀገራዊ ርዕያችንን ተጨባጭ ስኬት መመልከት ትልቅ ክብር ነው። ውጤት ተኮር አመራራችን ከዚህ ቀደም ታይቶ በማይታወቅ የኢንዱስትሪ መስፋፋት ተንጸባርቋል” ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማኅበራዊ ገጻቸው ባሰፈሩት ጽሁፍ ገልጸዋል።
በኤክስፖው ከ850 በላይ የንግድ ስምምነቶች እና ከ5 ቢሊየን ብር በላይ ግብይት ይፈፀማል ተብሎ እንደሚጠበቅ የኢንዱስትሪ ሚኒስትር መላኩ አለበል ቀድም ሲል ተናግረዋል።
"ኢትዮጵያ ታምርት ለሁለንተናዊ ሉዓላዊነት" በሚል መሪ ሀሳብ ከሚያዝያ 25 እስከ 30 ቀን 2018 ዓ.ም የሚካሄደውን አውደ ርዕይ፤ ከ150 ሺህ በላይ የሀገር ውስጥና የውጭ ዜጎች ይጎበኙታልም ተብሏል፡፡
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X