በአፍሪካ የመጀመሪያ የሆነ ዓለም አቀፍ የብስክሌት ውድድር በአዲስ አበባ እየተካሄደ ነው
17:01 03.05.2026 (የተሻሻለ: 18:16 03.05.2026)
ሰብስክራይብ
🌍🇪🇹 በአፍሪካ የመጀመሪያ የሆነ ዓለም አቀፍ የብስክሌት ውድድር በአዲስ አበባ እየተካሄደ ነው
— Sputnik Ethiopia (@sputnik_ethio) May 3, 2026
🚴🏼 የሲቲ ማውንቴን ባይክ ኢሊምኔተር (City Mountain Bike Eliminator) ፕሮ ሊግ ውድድር፤ ኢትዮጵያን ጨምሮ ከአፍሪካ፣ ከአውሮፓና ከእስያ ሀገራት የተውጣጡ ከ35… pic.twitter.com/VpmLEdrWP9
በአፍሪካ የመጀመሪያ የሆነ ዓለም አቀፍ የብስክሌት ውድድር በአዲስ አበባ እየተካሄደ ነው
የሲቲ ማውንቴን ባይክ ኢሊምኔተር (City Mountain Bike Eliminator) ፕሮ ሊግ ውድድር፤ ኢትዮጵያን ጨምሮ ከአፍሪካ፣ ከአውሮፓና ከእስያ ሀገራት የተውጣጡ ከ35 በላይ እውቅ ብስክሌተኞች ይሳተፉበታል።
የዓለም አቀፍ የሳይክሊስቶች ኅብረት እውቅና ኖሮት እየተካሄደ የሚገኘው ይህ ውድድር፤ በፒያሳ የዓድዋ መታሰቢያ ሙዚየም ዙሪያ 506 ሜትር ርቀት ይሸፍናል፡፡
በውድድሩ ይፋዊ መክፈቻ ላይ የተገኙት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ፤ “ውድድሮች ወደኛ እንዲመጡ እንፈልጋለን፤ ይህ መሆኑ ግንኙነትንና ዲፕሎማሲን ከማጠናከር ባለፈ ከዓለም ጋር ለመዛመድና ለመቀራረብ ያስችለናል” ብለዋል።
በተጨማሪም የአዲስ አበባን አዳዲስ መልኮች ከማስተወቅና የብስክሌት ስፖርትን ከማነቃቃት ባለፈ ከተማዋን የስፖርት ቱሪዝም መዳረሻ ማዕከል ለማድረግ እንደሚያስችል ተገልጿል ሲል የስፑትኒክ አፍሪካ ጋዜጠኛ ዘግቧል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X