የኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር 34 የመንገድ ፕሮጀክቶች ግንባታቸው ተጠናቆ በዚህ ዓመት እንደሚመረቁ አስታወቀ

ሰብስክራይብ

የኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር 34 የመንገድ ፕሮጀክቶች ግንባታቸው ተጠናቆ በዚህ ዓመት እንደሚመረቁ አስታወቀ

በአሁኑ ወቅት በመላ ሀገሪቱ ከ500 በላይ የመንገድ ግንባታ፣ ጥገና እና የዲዛይን ፕሮጀክቶችን እያከናወነ መሆኑንም ተቋሙ አስታውቋል።

የአስተዳደሩ ዋና ዳይሬክተር መሐመድ አብዱራህማን፤ ከ24 ዓመታት በፊት 26 ሺህ ኪሎ ሜትር ብቻ የነበረው የሀገሪቱ የመንገድ ሽፋን አሁን ላይ 180 ሺህ ኪሎ ሜትር መድረሱን ለሀገር ውስጥ ሚዲያ ተናግረዋል።

በአሁኑ ወቅት ከ55 በመቶ በላይ የሚሆኑት የግንባታ ሥራዎች በሀገር ውስጥ ተቋራጮችና ባለሙያዎች እየተከናወኑ እንደሚገኙ ገልፀዋል።

አስተዳደሩ በወሰን ማስከበር እና በግንባታ ዕቃዎች መወደድ ምክንያት ተቋርጠው የነበሩ 14 የመንገድ ፕሮጀክቶችን በበጀት ዓመቱ ዳግም ማስጀመሩም ተገልጿል።

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0