ኢትዮጵያ ባለፉት ሰባት ዓመታት የኤሌክትሪክ ኃይል የማመንጨት አቅሟን በሁለት እጥፍ አሳድጋለች ተባለ
13:01 03.05.2026 (የተሻሻለ: 13:18 03.05.2026)

ሰብስክራይብ
ኢትዮጵያ ባለፉት ሰባት ዓመታት የኤሌክትሪክ ኃይል የማመንጨት አቅሟን በሁለት እጥፍ አሳድጋለች ተባለ
የሀገሪቱ የኃይል ማመንጨት አቅም ከ4,462 ሜጋ ዋት ወደ 9,752 ሜጋ ዋት ማደጉን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል አስታውቋል።
የተቋሙ የኮሙዩኒኬሽን ዳይሬክተር ሞገስ መኮንን፤ የኤሌክትሪክ አገልግሎት ተደራሽነትም ከ44 በመቶ ወደ 54 በመቶ ማደጉን ለሀገር ውስጥ ሚዲያ ገልፀዋል።
ኢትዮጵያ በአሁኑ ወቅት 100 በመቶ በሚባል ደረጃ የኃይል ፍላጎቷን ከታዳሽ የኃይል ምንጮች (ከውሃ፣ ከንፋስ፣ ከጂኦተርማል) ማግኘቷ፤ በአፍሪካ ቀዳሚ የንፁህ ኃይል ማዕከል እንድትሆን አስችሏታል ብለዋል።
🪙 ሀገሪቱ በበጀት ዓመቱ ዘጠኝ ወራት ውስጥ ብቻ 24,970 ጊጋ ሰዓት የኤሌክትሪክ ኃይል በማመንጨት 90.16 ቢሊዮን ብር ገቢ አግኝታለች።
ኢትዮጵያ ለሱዳን፣ ለጂቡቲ፣ ለኬንያ እና ለታንዛኒያ ኤሌክትሪክ እየሸጠች ሲሆን ደቡብ ሱዳን፣ ሶማሊያ እና ሶማሊላንድም ፍላጎት እያሳዩ እንደሆነ ተመላክቷል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X