የአልጄሪያ ፕሬዚዳንት በቅርቡ በማሊ የተፈጸሙ የሽብር ጥቃቶችን ተቃወሙ

የአልጄሪያ ፕሬዚዳንት
የአልጄሪያ ፕሬዚዳንት  - Sputnik አፍሪካ, 1920, 03.05.2026
ሰብስክራይብ
የአልጄሪያ ፕሬዚዳንት በቅርቡ በማሊ የተፈጸሙ የሽብር ጥቃቶችን ተቃወሙ

አብደልመጂድ ታቡን በጎረቤት ሀገር እየሆነ ያለውን ሁኔታ በመኮነን፤ የአልጄሪያ እና ማሊን የተሳሰረ ወንድማማችነት አጽንኦት ሰጥተው አንስተዋል።

ከሀገሪቱ ብሔራዊ መገናኛ ብዙኃን ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ፤ አልጄሪያ በማሊ የተፈጠረውን ችግር "በትኩረት እና በገለልተኝነት" እየተከታተለች መሆኑን ተናግረዋል።

አልጀርስ "በማሊ የውስጥ ጉዳይ ውስጥ ገብታ አታውቅም፣ ወደፊትም ጣልቃ አትገባም" በማለት፤ የሀገሪቱን ወጥ ገለልተኛ አቋም በድጋሚ አረጋግጠዋል።

የሀገሪቱ መሪ ለሰላማዊ መፍትሔ ድጋፍ ለማድረግ ዝግጁ መሆናቸውንና አልጄሪያ ከአፍሪካ ሀገራት ጋር ሰላማዊ ትብብር ለማጠናከር ቁርጠኛ እንደሆነች ገልጸዋል።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X
አዳዲስ ዜናዎች
0