የሩሲያ "ህያው ክፍለ ጦር" ሂትለር ድል የተደረገበትን 81ኛ ዓመት በዓል ምክንያት በማድረግ በኪንሻሳ ሰልፍ አካሄደ

ሰብስክራይብ
የሩሲያ "ህያው ክፍለ ጦር" ሂትለር ድል የተደረገበትን 81ኛ ዓመት በዓል ምክንያት በማድረግ በኪንሻሳ ሰልፍ አካሄደ

በኮንጎ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የሚገኘው የሩሲያ ዲፕሎማሲ ሚሲዮን እንደገለጸው፤ አንዳንድ ሩሲያውያን በውጊያው የተዋደቁ ቀደምቶቻቸውን ምሥሎች፣ ባነሮችና ሰንደቅ ዓላማዎችን ይዘው ወጥተዋል።

ለስድስተኛ ጊዜ በተካሄደው በዚህ የመታሰቢያ ሰልፍ ላይ ኮንጓውያን ደጋፊዎችም አብረው ተሳትፈዋል።

ከተሳታፊዎቹ መካከል፦

🟠 የሩሲያ ዲፕሎማቲክ ኮር አባላት፣
🟠 በኮንጎ የሚኖሩ ሩሲያውያን፣
🟠 የውጭ ሀገራት ኤምባሲዎች ተወካዮች፣
🟠 በኮንጎ የተመድ የሰላም አስከባሪ ተልዕኮ ውስጥ የሚያገለግሉ የሩሲያ ፖሊስ መኮንኖች ይገኙበታል።

🪧 የሁለተኛው የዓለም ጦርነት የሶቪየት ተዋጊዎችን በሰልፍ የማሰብ ክንውን በሩሲያ የተጀመረው እ.ኤ.አ በ2018 ሲሆን አሁን ላይ በሁሉም አኅጉራት በየዓመቱ እየተከበረ ይገኛል።
በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X
አዳዲስ ዜናዎች
0